ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ እኔ 25 አመቴ ነው በገንዘብ እራሴን ለመቻል ከ 11በላይ የተለያየ የንግድ ስራ በግል እንዲሁም ከ 10 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች ጋር ትርፍ ለጋራ በሼር ስራ ሰርቻለው ግን ምንም ጠብ ያለልኝ ነገር የለም ሁሌም የሆነ እክል ይገጥመኝና ወይ በኪሳራ ወይ አዳዲስ በሚወጡ ህጎች ምክንያት ስራ ይበላሽብኛል የሰራሁት የሞባይል ካርድ ከመሸጥ እስከ ከውጪ ሀገር እቃ import እስከማድረግ ነው ግን አልሳካ አለኝ ስራ ለመልመድ ብዬ ሰው ጋር በነፃ 1 አመት ሙሉ ያለ ደሞዝ ሰራሁ አሁን በግል ስጀምር ስራው ጥምም አለብኝ እንደው ምን ባረግ ሊሳካልኝ ይችላል
Sep 01, 2022እስኪ አንድ ጊዜ በርከክ ብለህ ፈጣሪዬ ሆይ ስራዬን ባርክልኝ እኔ አቅቶኛል ካንተ የሆነ መባረክን ባርከኝ በለው::
Sep 02, 2022