For orthodox #ye kdase seat lay lenm be zema mehon asfelege lemn zm teblo ende wdase maryam aynebebm ? #endeza merzemu lemn asfelege ?
Sep 01, 2022ሦስት ሰዓት የሆነበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የቆየበትን ሰዓት ለማሰብ ነው
Sep 02, 2022For orthodox #ye kdase seat lay lenm be zema mehon asfelege lemn zm teblo ende wdase maryam aynebebm ? #endeza merzemu lemn asfelege ?
Sep 01, 2022ሦስት ሰዓት የሆነበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የቆየበትን ሰዓት ለማሰብ ነው
Sep 02, 20221ኛ- ቅዳሴም ሆነ ውዳሴ ማርያም ዜማ አለው፥ የሁለቱም ዜማ ደራሲ ራሱ ቅዱስ ያሬድ ነው። ውዳሴ ማርያም በቃል እንዲነበብ የተደረገው ዘውትር የምንጸልየው ጸሎት ስለሆነና በዜማ ከሆነ ስለሚረዝብን ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን ጊዜ ስለማይበቃን በሚለው እንጂ ለ7 ተከፍሎ ቀን ቀን የወጣለት፤ ውዳሴ ማርያም ይደገም የነበረው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነበር። 2- ቅዳሴ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ዜማ ቢኖረውም በዜማ የሚባለው ግን ጥቂት ቦታ ነው። እንደዛም ሆኖ ሰው ትኩረት አድርጎ የሚያዳምጠው ከንባቡ ይልቅ የዜማውን ነው። ለምሳሌ፦ ካህኑ ደጋግሞ "ማረን ይቅር በለን" ሲል ትኩረት ሰጥቶ የሚያዳንጥ የለም፥ ግን ቄሱ እጆቹን አንሥቶ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ብሎ በማያልቅ ዜማ መጸለይ ሲጀምር ግን የሚያውቀውን የማያውቀውም አፍ የተሰጠው ሁሉ ከካህኑ ተቀብሎ በዜማ ይጮኻል። ዜማ ከምናስበው በላይ በጣም powerful ነው፥ ሰው ከሐተታ ከተነገረው ይልቅ በዜማና በዘፈን ያዳመጠው more በልቡ ውስጥ ይሠርጻል። ውዳሴ ማርያምም ቢሆን በቃል ከሚባለው ይልቅ በዜማ የሚባለው ሆድን እያባባ ውስጥ ይሰርጻል። 3- እኔ ድሮ ቅዳሴ ረዥም ይመስለኝ ነበረ፥ ጣእሙን ከለመድኩት በኋላ ግን ታየኝ። ረዥም ሆኖ የሚታየን ቅዳሴን የምናስቀድሰው ከልባችን ስላልሆነ ነው እንጂ ጸሎተ ቅዳሴውን ከልባችን ብናዳምጠው ጸሎት ብቻ ሳይሆን ትምህርት መሆኑ ታውቆን ማለቁን ሳናስተውል ይደርሳል። 4ኛ- ቅዳሴ ዝም ብሎ ጸሎት አይደለም፥ የመሥዋዕት ማሳረጊያ ነው እንጂ። በዛች ዕለተ ዓርብ 9 ሰዓት ሙሉ እየተገረፈ፣ እየተመታ ተሰቅሎ የተሠዋውን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን በ2 ሰዓት ጸሎት ብቻ የምናሳርግበት ጸሎት ነው። ለዚም ሲባል ስሙ ራሱ "ሥርዓተ ቅዳሴ/ የመሥዋዕት ቅዳስል ይባላል። ቅዳሴ አስፈላጊነቱ ኅብስትና ወይኑን ወደ ጌታ ሥጋና ደም የሚለወጥበትና ህዝቡም ሥጋውን በልቶ ደሙን የሚጠጣበት እንደመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሳይገባን እና ሳይገባን በልተን በመለኮት እሳት እንዳንቃጠል (ቆሮ 11፥27) ሲባል ይህንን እንድንረዳ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ ለጸሎት መነሳት፣ ቅድስናውን መመስከር፣ ወንጌሉን ማድመጥ፣ ኃጢአታችን ማስታወስ፣ በኃጢአታችንም ይቅር እንዲለን፣ የምንበላው የምንጠጣው ምድራዊ መብል ሳይሆን ሰማያዊ መለኮት መሆኑን መረዳትና ማወቅ አለብን። የቅዳሴ ይዘት ባጠቃላይ ይህ ነው፥ ቅዳሴን የደረሱት (የጻፉት) ሌሎች ቅዱሳን ሳይሆን ራሳቸው ሐዋርያት ናቸው፥ የመጀመሪያ ቅዳሴም የቀደሱት እነሱ ራሳቸው ናቸው። ስናጠቃልለው እኛ በቅዳሴ የምንዳ'ኝ እንጂ ቅዳሴን የምንዳኝ አይደለንም። በመጨረሻ ከቅዳሴ አንቀጾች አንዱን ጠቅሼ ልጨርስ። ‟ሃሌሉያ በቅዳሴ ጊዜ ከምእመናን ወገን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ቢኖር ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገሥ፥ ከቊርባንም ባይቀበል ከቤተክርስቲያን ይለይ። የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምንም አቃሏልና። ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዳስተማሩን።” -ሥርዓተ ቅዳሴ አንቀጽ 3
Sep 02, 2022Tnxs alot
Sep 02, 2022" በመዝሙርና በዝማሬ #በመንፈሳዊ_ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ #ተቀኙና_ዘምሩ፤" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:19)
Sep 02, 2022Wedasemaraymem eko bezema nw yemnebebew egna senetseley zemi belen enanebewalen enje hulum yeyerasachew zema alachew
Sep 02, 2022https://youtu.be/SbFTJiNNlWE I think this will help u
Sep 02, 2022Ere mnteykew tyake eyawekn wegen ahun nbab hone zema hone lante mn yseralkal Abatochachn yhen yeseruln yerasachew mknyat slalachew nw Gn demo ke negere dhnet gar maygenagn tyake eyteyekn bantefa des ylegnal
Sep 02, 2022