Curse የሚለው እንግሊዝኛ ውስጥ በሁለት ቦታ ጥቅም ላይ ይውላል። አንደኛው በቁሙ "እርግማን፣ እገሌ ረገመኝ" ዓይነት በሚለው ከሆነ ያ ሰው እንደረገመው የሚሆን ነው። እንደዚ ዓይነት ያሉ እርግማን ከዛ ሰው ጋር የተያያዘ እንጂ ከመናፍስት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። የሰው እርግማን(በተለይ የእናት) ሥርን ይነቅላል ነው የሚባለው። ለዘር ያልፋል ግን በጸሎትና በምግባር ሊስተካከል ይችላል። ግን የመናፍስት እርግማን፥ ማለትም cursed family, cursed house ወዘተ የሚባሉ ከሆነ አዎ አለ ግን ወደ ልጅ የሚተላለፈው ልክ በደም እንደሚያልፈው ሆኖ ሳይሆን ልጁን በማኅጸንም ሆነ ከተወለደ በኋላ የሚናወጥ ነው። ይህ መናፍስት የሚናወጠው በተለያዩ መንገዶች ነው። 1ኛው ቤተሰቦቻቸው በፈቃዳቸው እርኩሳን መናፍስትን እና ጠንቋዮችን ሲገብሩ የነበሩ ከሆነ መናፍስቱ ከሚወልዱት ልጆች ጭምር አይርቁም። 2ኛው በስእለት ከሰጧቸው ደሞ ከበድ የሚለው የዛ ጠንቋይ ተተኪ ሊያደርገው የሚችለው መንፈስ ራሱ ሊያድርበት ይችላል። 3ኛ- ባእድ ነገር ይደረጉበት የነበረ ቦታ የምንኖር፣ የምንቅመጥ ከሆነም ይተላለፋል። 4ኛ- ደሞ በዘር ባይተላለፍም ልጆች ከተወለዱ በኋላ ልጆቻቸውን መናፍስትን ያለማምዳሉ (ከምሳሌ የቡዳ መንፈስ) ባጠቃላይ ይተላለፋል ግን ሚተላለፈው እንደ ደም እና እንደ ሥጋ ሆኖ ከሰው ተዋሕዶ አይደለን።
Sep 02, 2022