ስለ ቃለ ዐዋዲ የምታውቁት ነገር ካለ ስለ አስተምህሮት በምን ሀይማኖት ስር ናቸው አስተሳሰባቸውስ በማርያም አማላጅነትስ ያምናሉ የምታውቁትን ንገሩኝ pls
Aug 29, 2022በሀይማኖት አስተምህሮ ተሕድሶ ፕሮቴስታንት ሥር ናቸው። ነጠላ መልበሱና እጅ ማሸብሸቡ ኦርቶዶክስ ያስመሰላቸው ከሆነ በስተቀር በዶግማዊ አመለካከታቸው ሙሉ በሙሉ ከሙሉ ወንጌል ፕሮቴስታንት ጋር የሚለያየው ነገር የለውም። በሌላ ቋንቋ፤ በድንግል ማርያም፣ መላእክት፣ ጻድቃን ሰማዕታት አማልጅነትን አይቀበሉም፥ ክርስቶስን አማላጅ ይላሉ። ድንግል ማርያም ወላዲተ-አምላክ መሆኗን ይጠራጠራሉ። በዚህም ምክንያት በ2009 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ የጳጳሳት ጉባኤ "መናፍቃን" ብሎ አውግዟል። መዝሙራቸው ያው ከበሮና መሰንቆ መኖሩ አስመሰለው እንጂ ዜማቸውም፣ መሣርያ አጠቃቀማቸውም ሆነ ሽብሸባቸው ምንም ኦርቶዳክሳዊ አይደለም። Maybe ነጠላ ላይ ግን የሚለያይ የለም። ባጠቃላይ በኦርቶዶክስ ማልያ ለሌላ ቡድን የሚጫወቱ እንደማለት ነው።
Aug 29, 2022