Ishi wudoche ine milaw kiristian yemilaw lamindinaw matsaf kudus wust yaaltetsafe
Aug 27, 2022ክርስቲያን የተሰኘነው በክርስቶስ ነው። ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ተከታይ ክርስቶስን የለበሰ ማለት ነው።።በክርስቶስ ተፈጥሮ እንደ ክርስቶስ ኖሮ ስለ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ክርስቶስ የሚነሳና በክርስቶስ ቀኝ የሚቆም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለክርስቶስ ማንነት በዝርዝር አስቀምጧል በእሱ ስም በአባቱ ስምና በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነው ሚስጥረ ጥምቀትን የፈጸሙና መስቀሉን የተሸከሙ ክርስቶሳዊ ወይም ክርሰቲያን ይሰኛሉ። ክርስቶስ የሚለው ስም ለክርስቶስ ብቻ የተገባ እንደመሆኑ በስሙ ለሚያምኑና ሚስጥረ ጥምቀትን ለፈጸሙና ለተፈጸመላቸው ክርስቲያን የሚል ስምና ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። ይኽን ብቻ አይደለም በክርስቶስ ( በወልድ ) ያገኘነው። በዚኽም ለአብ ልጆቹ ስንሆን ለወልድ #ወንድሞቹ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎቹ እንደሆንን ልብ ይሏል። #ኦርቶዶክሳዊ_የተዋህዶ_ክርስቲያኖች የተላበሳችሁትን ጸጋና ስልጣን አስተውሉ። በእናንተ ላይ ያለውን መንፈስ ቅዱስ አታስመርሩት አታሽሹት። ይልቁንስ አዳፍነነዋልና ይሟሟቅና ይነድ ዘንድ ጾምን ጸሎትን ስግደትን አርምሞን ምጽዋትን ፍቅር ገንዘብ እናድርግ። #ንስሐ እንግባ። - መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን አይልም ላልከው ተሳስተሀል። መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ሲለን #ቤተ-ክርስቲያን ይለናል። ምሳሌ በሐዋርያት ስራ ላይ ስለተገለፀ ስለ ስለ ሳውል የቀደመ ግብር ተመልከት #ሳውል ግን ቤተክርስቲያንን ያፈርስ ነበር። ወደ ሁሉም ቤት እየገባ #ወንዶችንም #ሴቶችንም እየጎተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር። 8:3 ሲል ወደ ወኅኒ የሚወርዱትንና የሚሞቱትን ወንዶችና ሴቶችን ቤተክርስቲያን በማለት አስቀምጦልናል። ይኽ አሳዳጅ የነበረ ማር ጳውሎስ ይኽን ከተረዳ በኋላ በመልዕክቱ ለጵርስቅላና ለአኪላ ሰላምታ አቅርቡልኝ ካለ በኋላ እነርሱን የአህዛብም አብያተ ክርሰቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኗቸው ናቸው ብሏል እንዲም #በቤታችኹ ላለች ቤተ ክርሰቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ በማለት ለክርስቶሳዊያን ለክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን የሚል ስም ሰጥቶ ይታያል። ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ክርስቶሳዊ ውሉዳን . .እንባላለን።
Aug 28, 2022