Selam endet nachuh Mekureb lejemere wetat wechi hager hedo menoru krstnaw lay ftena ayametabetm blachu tasbalachu? Malet beteley Europe hager wst Orthodox church bdnb aygegnm ena endet nw ye neseha abat magegnet ymichalew plus ketrdachugn endet nw spiritual lifachnn meketl mnchlew ke tslot wechi yalutn mistratoch lemefetsem ykebdal siketl lemewdek bzu ngroch ygabzalu ketrdachugn ena eski hasab asteyayetachun ngerugn pls🙏🙏🙏🙏atlefut
Aug 26, 2022የትም ብትኖር በርግጥ ፈተና የማይቀር ቢሆንም በአንዳንድ ሀገራት ያሉት ሁኔታዎች ግን ለመንፈሳዊ ሕይወት የማይጋብዙ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። ግን ደሞ በፈተና መውደቅ በኛ ድክመት እንጂ ያሉት ሁኔታዎች እንቅፋት ሊሆኑን አይገባም። የትም ሀገር ብትሄድ እንደዚ ሀገር ብዙ ቅዱሳን መካናት እና አብያተ ክርስቲያናት አይኑሩ እንጂ እዛም እየኖርክ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ቅርርብ አጠንክረህ መያዝ የማይቻልበት ምክንያት የለም። ግን እንደዚ ያሉ ሀገራት ትንሽ ሊከብዱ የሚችሉት ላንተ ሳይሆን ነገ ለሚወለዱ ልጆች ግን ትንሽ ከበድ ሊል ይችላል። እኔ በማውቀው መሠረት አውሮፓ ሀገራት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናት አሉ፥ እነሱን ፈላልገህ መሄድ የሚቻል ቢሆንም በእንግሊዝ እና በግሪክ ሀገር ነው እንጂ በሌሎች ሀገራት እምብዛም ናቸው። ግን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ካልተገኘ የአኃት አብያተ ክርስቲያናትን በዶግማ ስለምንመሳሰል እዛ በመሄድ መቁረብና የንሰሐ አባት መያዝ ይቻላል። ለምሳሌ፥ ፈረንሳይ ወይም እንግሊዝ ከሆነ በግብጽ ሥር የሚተዳደሩ French Coptic Orthodox Church በመሄድ ቆርበህ ግብጻዊ መምህረ ንሰሐን መያዝ ትችላለህ። እንዲሁም ባሁን ሰዓት የሶርያ ስደተኞች አውሮፓ ውስጥ በመብዛታቸው የሶርያ ቤተክርስቲያንን (Jacobite Syriac Church of Orthodox)ን መሄድ ይህም ካልተገኘም የአርመንያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን በመሄድ ተመሳሳይ ሥርዓት እንዲፈጸመልህ ማድረግ ትችላለህ። ግን ማወቅ ያለብህ ቢኖር መንፈሳዊ ሕይወት እንደ ኢትዮጵያ አይቀልም።
Aug 27, 2022