Selam ye orthodox beteseboch yhen esti mlswln balachw ewkt or myak tykachw 1 sewe mn aln bale ena miste ke tgabw bwhala 1 akal sle myhonw be eswa/esw akal lay seltan Alachw blonal a priest alwn blo nw yngrn malt even eswa intercourse marg batflg esw ke flge gedetawa nw even ye ferd bet kesm hwla aysemwm alwn ...?ena mn ylal meshafw? 1 akal malt endy nw? Nesa fekads? -thanks in advance.
Aug 25, 2022ሁኔታውን እንድንረዳ ያክል ማወቅ ለምን እንደፈለግሽ በግልጽ ብትነግሪን ይሻል ነበር... በትምህርተ ክርስትና የባልና ሚስትን፤ ከቤተክርስቲያንና አገልጋይ ካህን ጋር ያመሳስሉታል። እንደ ሰው ስልጣነ ክህነትን ተቀብሎ ቄስ ሲሆን እንደ ድሮ ነጻ ሰው ሳይሆን የቤተክርስቲያን ገረድ ነው የሚሆነው። እንደ ድሮ በፈለገበት ሰዓት ወደፈለገበት መሄድ ሹመቱ አይፈቅድለትም። ቀድስ ሲባል መቀደስ፣ አድርስ ሲባል ማድረስ፣ አጥምቅ ሲባል ማጥመቅ በማይመቸው ሰዓትም ቢሆን ጊዜውን አመቻችቶ በፍቅር የማገልገል መንፈሳዊ ኃላፊነት አለበት። ነጻ ፈቃድ ይኑረው እንጂ ነጻ ፈቃዱን ለቤተክርስቲያን ማስገዛቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብር ያሰጠዋል። ይህም በወደ ትዳር ስናመጣው ከጋብቻ በፊት እሷም ሆነች እሱ የፈለጉትን የመወሰን፥ የፈለጉትን በራሳቸው መርጠው ማድረግ የሚችሉ ሰዎች ነበሩ። ጋብቻ ሲመጣ ግን አንዳቸው ለአንዳቸው የሚኖሩበት፥ ተስማምተው የሚዋሰኑበት የሚታጋገዙበት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው በፍቅር የሚታዘዙበት ነው። ድሮ በፈለጉበት ሰዓት ጓደኞቻቸውን ለማየት ይሄዱ ከሆነ አሁን ግን ለትዳር አጋራቸው ቅድሚያ የሚሰጡበት፥ የትም ቢሄዱ እሱ/እሷ በፈቀደበት/ችበት መጠን እንጂ እንደፈለጉ የማይሆኑበት ነው። ለዚህም ሲባል በትዳር ዓለም የባል ሥልጣኑ እራሱ ላይ ሳይሆን ሚስቱ ላይ ነው፥ ሚስቲቱም ስልጧና ባሏ ላይ እንጂ በአራሷ አይደለም። እንግዲህ ይህንን በሩካቤ ሥጋ(ግብረሥጋ) በኩል ስናየው...........የጋብቻ ዓላማ ከመጀመርያው አንዱ ሰው በሥጋው እንዳይፈተን ነው። ስለዚህም ነው ወደ ዝሙት እና ሌላ ፈተና እንዳይወድቁ ሲባል እንደ ባል እና እንደ ሚስት አብሮ መኖር መልካም የሚሆነው። በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሩካቤ የሚከለከሉበት ቀናት፥ ማለትም፦ 1) የወር አበባ ጊዜያት 2) በአራስነት ወራት 3) ጽንስ ከገፋ በኋላ 3) በሰንበት 4) በጾም 5) እና በዐበይት በዓላት፤ ከነዚ ከተዘረዘሩት ጊዜያት በስተቀር፣ በትዳር ሩካቤ የሚከልክል ሥርዓት የለም። ሆኖም በነዚ ጊዜያት አንዱ ላይፈልግ ይችል ይሆናል። ከዛ በላይ ግን ለምን አልፈለጉም የሚለውም አንዱ ጥያቄ ሊሆን ይችላል። "ህመም ነውን? ኩርፍያ ነውን? መፍራት ነውን? ፍትወት ማጣት ነውን?" የሚለው ቀዳሚ ጥያቄ ነው። ለዚ ጠቅላላ መልስ ሊሆን የሚችለው በግልጽ ተነጋግረው መረዳዳት መተጋገዝ፤ ራስ ወዳድነት የሌለው በፍቅር የሞላ ውይይትን ማድረግ ነው። በሷ በኩል ለምን እንዳልፈለገች ምክንያት ይኖራታል፥ እሱም እንደዛው። ምክንያቱ ቤተክርስቲያን ከመጥናት ጋር የሚያያዝ ከሆነ ለቤተክርስቲያኑ ሌላ ጊዜ አሳልፈው ለትዳር ቅድሚያ መስጠት ነው። ከህመምና ደዌ ጋር የሚያያዝ ከሆነ ደሞ እሱን መወያየት አስፈላጊ ነው። ግን ደሞ ያለምንም ምክንያት አለመፈልግ የትዳሩ ጤነኝነት አጣብቂኝ ውስጥ እያስገባ ይመጣል። ስለዚህ በህክምና መታከም የሚችል ከሆነ ጤና ባለሙያን ማማከር፣ ሌላ መፍትሄ ካለው ወደ ሌላ መፍትሔ መሄድ እንጂ just because of interest loss ከመሬት ተነስቶህ "መኝታችን ይገደም፤ በአንድ አልጋ እየተኛን እንመንኩስ" የሚባል ከሆነ የትዳር ሁኔታው አደገኛ እየሆነ ይመጣል። እሱም ሊያስብላት ይገባል፥ እሷም ልታሰብለት ይገባል። እኔም ነገሩን ማስረዳት እንዲቻለኝ በተቻለሽ መጠን የጠይቅሺበትን ምክንያት ብትገልጪልኝ፥ እዚ መጻፉም ከከበደሽ ደሞ በውስጥ መስመር ብታካፊይኝ ደስ ይለኛል።
Aug 26, 2022