ለፕሮቴስታንት ወንድሞቼ፧ ሰይጣን ይገድላሉ (በስጋም በነፍስም) ከእግዘብሔር ቤት ያርቃሉ ብላችሁ ታምናላችሁ? ካመናችሁ ፦ የእግዚአብሔር አገልጋይ ታዛዥ ለምን መላእክት ያድናሉ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባሉ ብላችሁ አታምኑም? ⏺ ሰይጣ የወደቀ መልአክ መሆኑ ሳይዘነጋ። መልሳችሁ በአመክንዮ ይሁን፤ አመሰግናለሁ!
Aug 25, 2022ሰይጣን ሕይወት የመስጠትም ሕይወት የመውሰድም ኃይል የለውም ። ሕይወትን የሚሰጥ ፣ የሚገድልም አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው ። ይህ ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር አምላክህን አምልክ እርሱን ብቻ ፍራ ባልተባለም ነበር ። ሰይጣን መዋሸት እና ማስመሰል ላይ ግን የተካነ የጨለማው አምላክ ነው ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ማንን መፍራት እንዳለብን ነግሮናል ' ስጋንም ነፍስንም በሲኦል ሊገድል ለሚቻለው እርሱን ፍሩ ፣ ስጋን የሚገድሉትን ግን አትፍሩ' በማለት ። እግዚአብሔር አምላክ የፈጠራቸው ድንቅ አድርጎ የሰራቸው ፣ ክብር ያላቸው ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው ። ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ሊያቀርበንም የተገባው ወይም ሊቤዠን ሚቻለው አንድያ ልጁ እርሱም እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ። ስለ መላእክት የእብራውያን መጽሐፍ በመጀመርያው ምእራፍ ላይ ያብራራልናል ። ስለዚህ አጋንንት ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች በኃጢአት እንዲወድቁ ይፈትነናል ፣ አዳምን እና ሔዋንን እንዳሳታቸው ሊያስተን ሀሰትን በጆሮአችን ይነግረናል ። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው ለእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ አብ የሰጠውን ማንም ከእጁ ሊነጥቀው የሚችል እንደሌለ ተናግሮአል ። የክርስቲያን መተማመኑም ይህ ነው ። ማንም ቢሆን ከአምላኩ ሚነጥለው አካል የለም ።
Aug 26, 2022