#የእመቤታችን_33ቱ_በዓላት 1 ጽንሰት ነሐሴ ፯ እመቤታችን የተፀነሰችበት 2 ልደት ግንቦት 1 የተወለደችበት 3 በአታ ማርያም ታህሳስ 3 በ3 ዓመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት 4 ታህሳስ 29 ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት መታሰቢያ 5 ጥር 21 እመቤታችን በ 64 አመቷ የአረፈችበት 6 የካቲት16 ከልጇ ታላቅ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት 7 የካቲት 21 ትከበራለች የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው 8 መጋቢት 21 የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው 9 መጋቢት 29 ትከበራለች ጌታችንን የፀነሰችበት ጥንተ በዓል 10. ሚያዝያ 21 የምትታሰብበት የግዝት በዓል 11. ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሀድ ተገልፃ ታላቅ ተአምር የአደረገችበት 12. ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡምንመናን በግለፅ በመታየት ታነጋግራቸው ነበር 13 ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ የገባችበት 14. ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት 15. ሰኔ 8 ተወዳጅ ልጇ ከደረቀ አለት ላይ ውሃ ያፈለቀበት ዕለት 16. ሰኔ 20 ጌታችን ተገልጦሐዋርያትን ሰብስቦ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ሰራላት 17. ሰኔ 21 ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው 18. ሐምሌ 21 ትከበራለች የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው 19. ነሐሴ16 ሥጋዋ የፈለሰበት በልጇ ኅይል ከሞት ተለይታ የተነሳችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ዕለት 20. ከነሐሴ17-ነሐሴ 21 ድረስ ለ5 ቀናት ትንሳኤዋ እንደ ልጇ ትንሳኤ ይከበራል የጌታ ትንሳኤ አንድ እሁድ ቀን መሆኗ የታወቀ ቢሆንም የትንሳኤው መታሰቢያ እስከ 50ቀናት ማክበራችንን እናስታውስ የእመቤታችንም እንደዚሁ ነው 21. ነሐሴ 18 የትንሳኤዋ መታሰቢያ 22. ነሐሴ 19 የትንሳኤዋ መታሰቢያ 23 ነሐሴ 20 የትንሳኤዋ መታሰቢያ 24. ነሐሴ 21 የትንሳኤዋ መታሰቢያ 25. መስከረም 10 ሥጋን የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራት ታደርግ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል ጼዴንያ ወደ ምትባል አገር ገብታ የተቀመጠችበትን ዕለት 26. መስከረም 21 ትከበራለች/ አርዮስን ለማውገዝ በ326ዓ.ም በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን ከሚያዝያ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ በመሆኑ የመስከረም ማርያም (ብዙኅን ማርያም ተብሎ በዓሏ ይከበራል እንዲሁም ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በመስከረም 21 ስላስገቡ ምዕመናን በዓሉን በግሸን ማርያም ያከብሩታል፡፡ 27. ጥቅምት 21 ትከበራለች የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው 28. ኅዳር 6 ወደ ግብፅ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት 29. ኅዳር 21 ጽላተ ሙሴ አክሱም ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት በክብር ያረፈችበት ዕለት ዳግመኛም ካህኑ ዘካሪያስ የእመቤታችን ምሳሌ የሆነውን የምቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት 30. ታኅሣሥ 21 ትከበራለች የምትታሰበት የግዝት በዓል ነው 31 ታኅሣሥ 22 ብስራተ ገብርኤል(ቅዱስ ድቅስዮስ እመቤታችን ጌታችንን የጸነሰችበትን መጋቢት 29 ቀንን በዚህች ዕለት አከበረ፡፡ 32. ታኅሣሥ 28 ጌታችንን የወለደችበት መታሰቢያ ዕለት በ4 አመት አንድ ጊዜ ወርሃ ጷጉሜን 6 ስትሆን ልደት በ28 ይውላል፡፡ 33. ታኅሣሥ 29 ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት መታሰቢያ በዓል •➢ ሼር // SHARE @Mezmure_tewahdo @Mezmure_tewahdo
Aug 23, 2022