Selam sewochye አንዲት ያላገባች ቆራቢ ወጣት ማግባት ምትችለው ድንግል ወይም እንደሷ ቆራቢ ወንድ ብቻ ነው ?ወይስ ድንግል ያልሆነ ወይም ቆራቢ ያልሆነም ማግባት ትችላለች?
Aug 20, 2022#1 ጋብቻ የሰው ልጅ ለሰማያውዊ መንግስት ከሚበቃበት መንገዶች ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ ክቡር ሲያሰኘው ይኽ ክቡር ሕይወት ደግሞ መኝታው ንፁህ መሆን ይኖርበታል። #ኦርቶዶክሳዊያን ልናስተውለውና ልናውቀው የሚገባ ነገር ቢኖር ከስርዓተ ቤተክርሰቲያን ውጪ ማለትም ከተክሊልና ከቁርባን ውጪ በዓለማዊ ስርዓት የሚፈፀምን ጋብቻን እግዚአብሔር እንደማያውቀው ነው። እግዚአብሔር ጋብቻችንን እንዲባርክ በትዳራችንም መልካም ፍሬንም እንድናፈራበት በመንገዱ መሄድ እንዳለብን ማስተዋል ይገባል። #2 ቁርባን አለመቁረብ ለክርስቲያን መብቱ አይደለም። መቁረብ ለክርስቲያን መንፈሳዊ ግዴታው ነው። በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስርዓት መሰረት በሰንበተ ክርስቲያን ክርስቶሳዊያን ቅዳሴን አስቀድሰን የመቁረብ ግዴታ አለብን። የቻለ በሳምንት ያልቻለ በወር አልያም በበዓላት ከዛም ያልቻለ ቢኖር በዓመት 3 ግዜ የመቁረብ ግዴታ አለብን። እንደ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ጥንት የቅዳሴ ጸበል ለቆራቢያን ብቻ ለአፍ ማደፊያነት የተገባ ነበር ምክንያቱም አስቀድሶ የማይቆርብ ስላልነበር ። በዚኽ አጋጣሚ የቅዳሴ ጸበል ማታ ከ3ሰአት በኋላ ምግብ በልታችሁ የምትጠጡት አይነት ጸበል አይደለም እጅ ላይም ማፍሰስ ተገቢ አይደለም ቤተክርስቲያን ከስጋወ ደሙ የራቅን ልጆቿን ተስፋ እንዳንቆርጥና ወደ ስጋወ ደሙ እንድንቀርብ የቅዳሴ ጸበልን ብትፈቅድልን ያልተገባ ነገር ማድረግ መልካም አይደለም። ይኽን ከማድረግ ተቆጠቡ። እንግዲ ለአንድ ክርስቲያን መቁረብ ግዴታው እስከሆነ ድረስ ትዳሩም በስርዓተ ቁርባን ሊሆን እንደሚገባ ልብ ይሏል። አንዲት ያላገባች ቆራቢ ወጣት በመቁረቧ ክርስቲያናዊ ግዴታዋን እየተወጣች እንደመሆኑ መልካም ነው የሚያስታብይ አልያም የሚያኮራ ነገር ግን የለውም ፍጻሜው እንዲያምር መለመን እንጂ። ይቺ ሴት ልታገባው የወደደችው ወንድ ድንግል ቢሆንም ባይሆንም ችግር የለውም ችግር የማይኖረው ግን ልታገባው የፈቀደችው ሰው በስጋወ ደሙ ታትሞ የመኖር አላማ እስካለው ድረስ ብቻ ነው። ቀድሞ የቆረበ ከሆነ መልካም ካልሆነ ከጋብቻችሁ እለት አንስቶ እስከ ሰማንያችሁ(እስከ ዕለተ ሞታችኹ) ድረስ በጋራ እየቆረቡ በህገ እግዚአብሔር ፀንቶ የመኖር አላማ ካለው ቀድሞ አለመቁረቡም ችግር አይሆንም። ድንግል የሆነ አልያም ያልሆነ ቆራቢ የሆነ አልያም ያልሆነ ነገር ግን ቆራቢ የሚሆን መንፈሳዊ ሕይወቱ የተፈተሸ ሰው ታገባ ዘንድ ይገባታል። በስሜት ለሴቷ ሲሉ አልያ ለወንዱ ተብሎ በቁርባን ጋብቻ እየተፈጸመ በኋላ ከስጋወ ደሞ እየራቁ እጅግ በከፋ ኃጢአት ውስጥ የተዘፈቁ እልፎች አሉ። #ዓላማና #ጥንቃቄ ይኑረን።
Aug 21, 2022