የፀሎት መፅሀፍ አደጋገም ሥርዓት ብትነግሩኝ malt be eyeltu selot sarg yetun kfl lanbeb
Aug 18, 2022[Forwarded from በማለዳ ንቁ !] ሰባቱ የጸሎት ሰዓታትና የሚጸለዩት ጸሎቶች ➊• ነግሕ፦ጠዋት 11:00 ሰዓት ወይንም (በፈረንጆቹ 5:00 AM) የሚጸለዩት ጸሎቶች ☞ ውዳሴ ማርያም፣ ይዌድስዋ መላእክት፣ ሠይፈ ሥላሴ፣ ሠይፈ መለኮት ☜ 🌺 ጠዋት 11:00 አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አምላክን በፀሎት የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር) ✔️ እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሃን እንድናይ ስላበቃን በዚህ ሰዓት እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም በዚህ ሰዓት ጌታችን ለክስ ከጲላጦስ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰዓት ስለሆነ፤ በዚህ ሰዓት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት የተባረረበት ሰዓት ስለሆነ፤ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ ታዝዋል፡፡ ➋• ሦስት ሰዓት ጠዋት 3:00 ሰዓት ወይንም (በፈረንጆቹ 9:00 AM) ☞ አርጋኖን ፣መልክአ ገብርኤል፣ መዝሙረ ዳዊት ☜ 🌺ሰልቱ ሰዓት ከጠዋቱ 3 ሰዓት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር) ✔️በዚህ ሰዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ ገብርኤልን የሰማችበት ሰአት ስለሆነ፤ አንድም በዚህ ሰዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን የጸነሰችበት ሰዓት ስለሆነ፤ አንድም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት ስለሆነ፤ እያንዳንዱ ክርስቲያን ይሄንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግን ታዝዋል፡፡ ➌• ስድስት ሰዓት (ጊዜ ቀትር) 6:00 ሰዓት ወይንም (12:00 PM በፈረንጆች) ☞ መልክአ ሚካኤል፣ መልክአ ሥላሴ ☜ 🌺 6:00 አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ 6 ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር ) ✔️ ጌታችን በቀራኒዮ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና፤ አንድም ልብሱን ተገፎበታል፤ አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታልና፤ በሌላም ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሰዓት ክፉ መናፍስትን አሸንፎ ጥሎበታልና አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል፡፡ ➍• ዘጠኝ ሰዓት ከሰዓት 9:00 ሰዓት ወይንም (3:00 PM በፈረንጆች) ☞ መልክአ መድኃኔዓለም፣ መልክአ ዑራኤል ☜ 🌺 ተስአተ ከ ቀኑ 9:00 ሰአት ሲሆን አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት ምክንያት (ሚስጥር) ✔️ አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መራራ ሐሞት አጠጥተውበታል፤ አንድም ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው የለየበት ሰአት ነውና፤ አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን አፅርሐ መስቀል የተናገረበትና ቅዱስ ዑራኤል ከጎኑ ውጋት ደም በዋንጫ ቀድቶ ዓለም ላይ የረጨበትም ነውና፤ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበን እንዲጸልይ ታዝዋል፡፡ ➎• ሰርክ፦አስራ አንድ ሰዓት 11:00 ወይንም (5:00 PM በፈረንጆች) ☞ መልክአ ፋኑኤል፣ ውዳሴ ማርያም፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ የሠርክ ጸሎት፣ የምኅላ ጸሎት ☜ 🌺 የሰርክ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይበት የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር) ✔️ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር የወረደበት ሰአት ስለሆነ፤ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ ምስጋና ስለሚገባው ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ ታዘዋል፡፡ ➏• ጸለፀተ ንዋም ማታ 3:00 ሰዓት ወይንም (9:00 PM በፈረንጆች) ☞ አርጋኖን፣ መልክአ ሩፋኤል ☜ 🌺 ከምሽቱ 3 ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲያመሰግን የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር) ✔️ በዚህ ሰዓት እራሱ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስርአተ ጸሎት አሳይቶበታልና፤ አንድም በዚህ ሰዓት ጌታችንን አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት ተረበርበው የያዙበት ሰዓት ስለሆነ፤ አንድም በዚህ ሰዓት አንድ ክርስቲያን ከመተኛቱ በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ መተኛት አለበትና ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲጸልይ ታዝዋል፡፡ ➐• እኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ወይንም (12:00 AM በፈረንጆች) ☞ መዝሙረ ዳዊት፣ መልክአ ሥላሴ፣ መልክአ ሚካኤል፣ ሰይፈ ሥላሴ ዘወትር ☜ 🌺 መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር) ✔️ በዚህ ሰዓት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶበታልና፤ አንድም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎበታልና(ተነስቶበታልና)፤ በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ ሌሊት እነሳለው ባለውም መሠረት ለምስጋና እንቆማለን፡፡
Aug 19, 2022