#religion
#for Orthodox ሰላም ለእናንተ ይሁን ጥያቄዬ ለቅዱሳን የፀጋ ስግደት እንደሚገባ ቤተክርስቲያን ታስተምራለች እና ይሄንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ብታስረዱኝ
Aug 15, 20223 engagements
#for Orthodox ሰላም ለእናንተ ይሁን ጥያቄዬ ለቅዱሳን የፀጋ ስግደት እንደሚገባ ቤተክርስቲያን ታስተምራለች እና ይሄንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ብታስረዱኝ
Aug 15, 2022አስቀድሞ ቅዱሳን የተባሉ እነማን ናቸው ክብራቸው ምን ድረስ ነው ተጋድሎአቸው ምን ይመስላል የሚለውን ሰው ከጠነቀቀ ስግደት ይገባቸዋል አይገባቸውም የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ሳይሻ በአይምሮ ጠባይ ስግደት ይገባቸዋል አይገባቸውም የሚለውን መመለስ ይቻለዋል። ምክንያቱም ቅዱሳን ከመጽሐፍ ቅዱስ በፊት የነበሩና መጽሐፍ ቅዱሱም የተጻፈው በቅዱሳኑ ላይ ባደረ መንፈስቅዱስ እንደመሆኑ ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ መፈለጉ እውቀትን ለማጽናት ካልሆነ በቀር በአማን ስግደት እንደሚገባቸው የታወቀ የተገለጠ ነው። ለጥያቄኽ ምላሽ ግን የሚከተሉትን ጥቅሶች መመልከት መልካም ነው። 1ሳሙ 28:14 2ነገ 2:15 ዳን 2:46 ዳን 8:15 መሳ 13:20 ኢያ 5:13 ዘኁ 22:31 1ዜና 21:21 ሐዋ 10:25 ራዕ 3:9 ሌላም መዘርዘር ይቻላል።
Aug 17, 2022