ከማፈቅራት ልጅ ጋር እንዴት መለያየት እችላለው? አሁን አብረን ነን እሷ ግን ለኔ ግድ የላትም እና እንዴት እሷን መጥላት እንደምችል ንገሩኝ እባካቹ።
Aug 11, 2022እሷም እንዳንተ የምትወደው ሰው ይኖርና ልባቹ ለየቅል ሆኖ ይሆን!! ፍቅር በአንድ ወገን ብቻ ከሆነ ሙሉ አይደለም!! የትምም አይደርስም። ስለዚህ በቻልከው መጠን ካሁን ከነበረክ ቀረቤታ እና እሷን በማባበል የምታጠፋውን ጊዜ በሌላ ነገር እና የህይትህን መስመር በሚያስተካክልልክ ነገር ላይ ለማጥፋት ሞክር (ከሷጋር የምታሳልፈውን ጊዜ ቀንስ) እድለኛ ከሆንክ ወዳንተ ልትመለስ ትችላለች ካልሆነ ግን መስመርህን ሳትስት እየተንገዳገድክም ቢሆን ወደኋላ ሳታይ ጉዞህን ቀጥል ከሷ የተሻለ ሌላ የልብህ ንግስት ታገኝ ይሆናል ማን ያቃል ፣ መንገድህን የምታሳምር ሴት ከፊት ቀደም ብላ እየጠበቀችህ ሊሆን ይችላል!! የራስህ ባልሆነው ነገር ላይ ብዙ አትታገል ትርፉ ልፋት እና ውዷ ጊዜክን ማቃጠል ነው። ወንድሜ ጊዜህን ተጠቀም ህይወት አጭር ናት።
Aug 14, 2022