"ፆም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው።ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙንየሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነእግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታየሚሠራበት ጊዜ ይሆናል። ፆም ማለት ነፍስና ስጋበኅብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናወን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። በፆም ወቅት ነፍስን ሥጋ የነፍስን ሥራለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት ለፀሎት ለተመስጦ ለክብርናከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትንለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው።"
Aug 11, 2022