“አግሪጳም ጳውሎስን፦ በጥቂት ክርስቲያን ልታደርገኝ ትወዳለህ አለው።” — ሐዋርያት 26፥28 “ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።” — ሐዋርያት 11፥26 “በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥6 “ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።” — 1ኛ ጴጥሮስ 4፥16
Aug 09, 2022