ሰላም ቤተሰቦች በጣም ጨንቆኛል እባካችሁን አግዙኝ ልጅቷን የሆነ ቦታ ነበር ያየኋት ስልኳን ወስጄ ለ 3 ሳምንት አወራንና በሰዓቱ በጣም ፍላጎት ነበራት ቀጥሬያት በአካል ተገናኘን ከዛ እየወደድኳት መጣሁ እሷ ደሞ ተቀየረችብኝ እንደሴትነቷ መግደርደሯ ነው ብዬ በጣም ቀረብኳትና ሳላስበው ከባድ ፍቅር ውስጥ ገባሁ እሷ ግን ትርቀኝ ጀመር ሜሴጅ አትመልስም አንዳንዴም ስልኬን አታነሳም 4 ወር ሆኖታል በጣም ሲጨንቀኝ እንዳፈቀርኳት ነገርኳት ለውጥ የለም እንደውም ባሰ ፍላጎት እንደሌላት ገብቶኛል ግን መርሳት ከበደኝ በጣም ነው የምወዳት አውቃለሁ አጭር ግዜ ነው ግን አሁን ላይ የማስበው ስለሷ ብቻ ነው ስራ መስራት ከብዶኛል ሕይወቴን መኖር አቅቶኛል ውሎዬ ቤተክርስቲያን ነው ከዛ ውጭ ሌላ ነገር ሁሉ አስጠልቶኛል ምን ላርግ?
Aug 08, 2022ቤተክርስቲያን የምትውል ከሆነ ጊዜህን መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ፣ ሰው በመጠየቅ ወይ በማስተዋል ብቻ በሚሰራልህ መንገድ ፍቅር ምን እንደሆነ ለመረዳት ሞክር። አሁን ያለህበት ሁኔታ እውነት ፍቅር ነው ወይ የሚለውንመ እንደዛው። ይቅናህ።
Aug 09, 2022