ሰዎች ቆይ በቃ አይቻልም እንዴ? ከማስተርቤሽን ሱስ መላቀቅ? ብዙ ብዙ ሞከርኩ ግን ተስፋ አስቆራጭ ነው የተሳካለት ካለ ብቻ ይንገረኝ ሄዳችሁበት ማታቁትን ሂወት እንዲ አድርግ እንደዛ አድርግ እንዳትሉኝ
Aug 05, 2022የማታውቁትን ሕይወት እንዲኽ አድርግ እንዲ አታድርግ እንዳትሉኝ ማለትኽ ለመተው ፈልገኽ ነገር ግን ፈተናው ከብዶብኽ እንደሆነ ብረዳም ላንተ ግን ከዚኽ መንገድ እንድትለይ የግድ በዛ መንገድ ያለፉ ሰዎችን ብቻ መፈለግኽ ትክክል አይደለም። ፈተናውን ለመረዳት ዲያቢሎስን ማወቅ በቂ ነው። እሱ አንተንመወ ሆነ ሌሎቻችንን ነፍሳችን በእጁ እስኪያገባት ድረስ የፈተናን መልክ እየለዋወጠ አሳራችንን ያበላናል #እንቢ ማለት ስንጀምር ግን ከእኛ ይርቃል። ለእግዚአብሔር ተገዙ ዲያቢሎስን ግን ተቃወሙ(እንቢ በሉት) ከእናንተም ይሸሻል እንዳለን ሐዋርያው። እግዚአብሔር ቅዱሳኑን በዘማዊያን ላይ አስተምሮአቸዋል። ስለዚኽ አስቀድመኽ ከማንም ቢሆን ምክርን ለመቀበል ተዘጋጅ በጎውን ከፍሬው ታውቀዋለኽ መርጠኽ የአንደበቱን መልካም ፍሬ ለመብላት ተዘጋጅ የማታውቁትን ሕይወት እንዲ አድርግ እንዲ አታድርግ እንዳትሉኝ የሚል ሀሳብን ከጭንቅላትኽ አውጣ። አንድ ሰው ግለ ወሲብ እየፈጸመ Wonder ይኽን ተግባር አትፈጽመው ከእግዚአብሔር አጣልቶ ጎስቋላ ያደርግሀል ቢልኽ ትክክል ነው አይደለም ? አንደበቱ ትክክል ነው። ግብሩ መልካም እንዳልሆነ እያየኽ ግን አይ እሱ እያደረገው አይደል እኔ ለምን አላደርገውም የምትል ከሆነ አልያም አንተ እኔን ለመምከር ብቁ አይደለኽም ብለኽ የወንድምኽን ኃጢአት ከተመለከትክ ትክክል አይደለኽም እነዚኽን ከልብኽ ማውጣት ይኖርብሀል። ግብረ አውናኑን በተመለከተ ግን አንዳንድ የምታናግሩኝ ወንድም እህቶቼም ጨምሮ የዘነጋችኹት አንድ ነገር አለ ይኸውም ከመምሕራን ከመጽሐፍት ከመንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች ከማንኛውም በጎ ነገሮች ሁሉ የምናገኘው በጎ ምክር መንገድን ይመራናል እንጂ አይጓዝልንም። ከዚኽ ፈተና ጋር አያይዤ ምሳሌ ልስጥኽ። ዲያቢሎስ ሆን ብሎ እስኪትህን እንዲበላኽ ያደርግሀል በዚኽ ሰአትም ታክከዋለኽ በምታከው ሰአት ይህ ጾር ተነስቶብኽ ራስኽን ማጎሳቆል ትጀምራለኽ ስለዚህ መጽሐፈ መነኮሳት እንዲ አለ ብልትህን ቢያሳክክኽ አትከከው። #አለማከክ_ያንተ ድርሻ_ነው_መጽሐፉ_አያክልክም ። አታድርግ የተባልከውን አታድርግ። እንባህ ይመጣል ያዛጋሀል ያስለቅስሀል ያነጫንጭሀል ከሰው ያጣላሀል ፈጣሪኽን እስከ መስደብ ያደርስሀል ዘመዶችህን ለወሲብ እስከመመኝት ይፈትንሀል በቁምኽ አይደለም ተኝተኽ እንኳ የማይተኛ ይፈትንሀል ከባድ ነው #ግን #እንቢ_በለው ከአንተ ይርቃል። በአማን የሐዋርያው ቃል የታመነ ነው። አንዳንዶች ምን ላርግ ትላላችኁ እሰየው መልካም መጠየቃችኹ በሉ በመጠን ተመገቡ ሲባል እንብርት ቦታውን እስኪለቅ ትበላለኽ ስገዱ ሲባል ብረት ለመግፋት የነበረኽ አቅም 41 ለመስገድ ታጣዋለኽ በል እንዲኽ ይኽ ሀሳብ ሲመጣብኽ ብቻኽን አትሁን ሰትባል ዲያቢሎስ ፈተናውን ጠንከር ሲያረግብኽ ካለህበት ካፌ እንኳ ተነስተህ ሽንት ቤት ሄደኽ ትፈጽመዋለኽ። ከዲያብሎስ ጋር ውጊያ ውስጥ እንዳለኽ አስታውስ እስኪያሸንፍኽ ይዋጋሀል እስኪማርክህ ይፈትንሀል። ውጊያ ውስጥ መሆንኽን ዘንግተኽ ከተማረኽ መሸነፍኽ የማይቀር ነው ጠላት እጅ የገባ ተዋጊ መሞቱ መጎሳቆሉ አይቀርም። ላለመማረክ ታገል። ላለመሸነፍ ቁረጥ። አሸናፊው አምላክ ለማሸነፍ ቆርጠኽ ከተነሳኽ ይረዳሀል። ዛሬ ነገ አትበል የመዳን ቀን ዛሬ ነው ይልሀል ሐዋርያው ዛሬ ለማቆም በሀሳብ ቁረጥ። እንቢ በል። ይኽን ግብር በእጅኽ አይደል የምትፈጽመው ? እጅኽ በፍጹም ብልትኽን እንዳይነካ በዛ መንገድ እንዳይነካ ጠብቀው። ይኽኔ ጫን እያለ ይሄዳል አይምሮኽን ሀሳብኽን እየተቆጣጠረ ያስጨንቅሀል ታገለው በፍጹም ተሸንፈኽ እጅኽን ወደ ብልትህ አትስደድ። ይኽ ያንተ ድርሻ ነው። የሀሳብ ውጊያውን በበጎ ሀሳብ ተዋጋው። ይኽን እንድታስብ ካረጉህ ነገሮች ሁሉ እራቅ ጆሮኽን ዐይንኽን እነዚን መጠበቅ ያንተ ድርሻ ነው።
Aug 06, 2022