ለኦርቶዶክሳዊያን ብቻ። #ዘላለም_ሥላሴ። እንዴት ዋላችቻኁ ? 1.ሀይማኖታዊ ጥያቄን በዚኽ ቻናል የምትጠይቁት ለምንድነው ? 2.የሚመልሱላችኹ ሰዎችስ በእውን ኦርቶዶክስ ናቸው ? ምክንያቱም ከምመለከታቸው ምላሾች ውስጥ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ስለምመለከት 1.ሆን ብለው 2.ከእውቀት ማነስ 3. ለምንድነው ቤተክርስቲያን ሄዳችኹ በሰንበት ት/ቤት በማኅበራት በጉባኤ የሚሰጡ ትምህርቶችን የማትከታተሉት ? 4.ሀይማኖቴ ፍፅምት ንፅህት ናት ብላችኁ በእውን ከልብ ታምናላችኹ ? ካመናችኹ ጥርጣሬ ከአይምሮአችኹ ተነስቶ ከልባችኹ ሊያድር ሲዳዳ ምንድነው የሚያርበተብታችኹ ? ከእናንተ አለማወቅ እንጂ ከሀይማኖቷ እፀጽ እንደሌለ ለምን ለልባችኹ መንገር ያቅታችዃል ?
Aug 01, 20221.ይኽ ቻናል ማንኛውንም ጥያቄ ስለሚያስተናግድ 2.ጥያቄው ላይ ለመሳተፍ የፈለገ ሁሉ መመለስ ይችላል። መልሱን ይዞ መምህራን ጠይቆ፣ መጽሐፍ አገላብጦ መረዳት የጠያቂው ስለሆነ 3.ሁላችንም ምክንያት ይኖረናል ብዬ አምናለው (ስንፍናን ጨምሮ) 4.ጥርጣሬ ያለበት ካለ (በማንኛውም ኃይማኖት) ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል። እውነት ነው አንዳንዴ ምንም የተጨበጠ እውቀት ሳይኖረን ጥያቄው ሊቀድም ይችላል፤ ሌላው የዚህ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመንም በዚህ ሊከፋ አይገባም! ግን ኃላፊነቱን ተወጥቶ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት እንጂ። ባይሆን ከጠያቂዎች አንዳንድ ነገር የታዘብኩት የዚህ ኃይማኖት ተከታይ ነኝ ብለው ጥያቄያቸውን ስለሚጀምሩ፤ ጥያቄያቸው የዛ ኃይማኖት ተከታይ ሁሉ ጥያቄ የሚመስልበት ጊዜ አለ። ያ ሊስተካከል ይችላል። በደፈናው ኃይማኖቴ ልክ ነው መጠየቅ አይገባኝም ማለት ግን ያለበን አይመስለኝም።
Aug 02, 2022