ሰላም ቤተሰብ እርዱኝ አትለፉኝ በእናታችሁ አንድ ጓደኛዬ የስምንተኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ተበላሸበት ። ልጁ ጎበዝ ተማሪ ነው። በአንደኛው ሴሚስተር 8ኛ ነበር የወጣው ። መምህራኖቹንም ስጠይቃቸው በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው እኮ አሉኝ ። የማለፊያ ነጥብ 39 ተብሎ እሱ አመጣ የተባለው 38.6 ነው እና እንዴት ነው ቅሬታ የምናስገባው? የቅሬታው ነገርስ ምንም ለውጥ ከሌለው እንዴት ብዬ ካለበት ሀዘን እና ጭንቀት (መጥፎ ሁኔታ) የማወጣው እና እንዴትስ አድርጌ ውጤቱን በፀጋ ተቀብሎ የሚቀጥለውን አመት እንዲማር የማደርገው እሱ አሁን የሚያስበው መጥፋት እራሱን መጉዳት ነው እና እንዴት አድርጌ ልርዳው ላሳምነው ? በጣም አመሰግናለሁ
Jul 29, 2022እመቤቴ ታፅናናው:: ምንም ፈተናው ቀላል ቢሆንም ገና ልጅ ነው እና ለዚህ የሞተ ካሪኩለም ገና በልጅነቱ ተስፋ መቁረጥ አይገባውም:: ቤተ ክርስቲያን ውሰዱት በቄስ አስመክሩት
Jul 29, 2022