Ortodox brazeroch and sisters manew be thtna ehen ngr miasredagn “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” — ዮሐንስ 5፥30 And this “እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤” — ዮሐንስ 5፥31 Amesegnalew lemelsachu
Jul 29, 2022ጥቅስን ቆራርጦ ማመጣት ትክክል አይደለም እንደዚ ነው የሚለው ‟እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ 'ሰማሁ' 'እፈርዳለሁ' ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤ ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ 'የሚመሰክረው' ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።” ዮሐንስ 5፥30-32 ምስጢረ ሥላሴን ነው፥ ስለሥላሴ የኩነት ነው የሚናገረው። አብ-ልብ፣ ወልድ-ቃል፣ መንፈስ ቅዱስ- እስትንፋስ የሚለውን? በአብ ልብ ያለውን ወልድ ይናገራል መንፈስ ቅዱስ ይተገብራል/ይመሰክራል። አብ የፈቀደው በልቡ ነው። ወልድ ደሞ የልብን በቃሉ ይፈርዳል፥ መንፈስ ቅዱስ ደሞ ቃሉን ይመሰክራል። ነገረ-ሥላሴና ነገር-ክርስቶስን በተወሰነው ካልተረዳህ ትንሽ ውዝግብ ይልብሃል።
Jul 29, 2022