Let assume you are a girl. ለሱባኤ ከሆነ የገዳሙን ሥርዓት መጠበቅ ብቻ በቂ ነው። ለምንኩስና ከሆነ ግን በጣም ከባድ ነው። መጀመርያ እራስን ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ማረግ አስፈላጊ ነው። ገዳም መግባት ያለብሽ ዓለም ክዶሽ፣ ኑሮ ከንዶሽ ሳይሆን ዓለምን ክደሽ፣ ምቾቱን ድሎቱን ንቀሽ መሆን አለበት። ከዛ በፊት ቅድመ ምንኩስና በዓለም እያለሽ በጾም፣ በጸሎት፣ በሱባኤ መበርታት አለብሽ። ከዛ በመቀጠል ለምንኩስና ዝግጁ መሆንሽን አርግጠኛ ስትሆኚ ንብረት ካለሽ ንብረትሽን ሁሉ ሽጠሽ ለድኆችና ለተቸገሩት መጽውተሽ ወደ ወሰንሽበት ገዳም ወይም ቤተደናግል ሄደሽ ምኞትሽን ትነግሪያቸዋለሽ። እነሱም ብዙ ምክርና ትግሣጽ ከሰጡሽ በኋላ ዳግም ፍላጎትሽን ይጠይቁሽና ለመመንኮስ ፍቃደኛ ከሆንሽ ጸጉርሽ ይላጭና የገዳሙ አገልጋይ ትሆኚያለሽ፥ ከወራት በኋላ ሥርዓተ ምንኩስና ተፈጽሞልሽ ሙሉ የእግዚአብሔር ጃንደረባ መነኩሲት ትባያለሽ። ከሁሉም በፊት ግን ሃሳብሽን ደግመሽ ደጋግመሽ አስቢበት።
Jul 25, 2022