የ መጀመሪያ አመት የማስተርስ ተማሪ ነኝ እና የ እንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዬ ከ ማስተረስ ተማሪ የሚጠበቅ አይደለም እንዴት ማሻሻል እንደምችል ጠቁሙኝ እባካቹ
Jul 21, 2022ኢንግሊዝኛውን ለመረዳት ብሎም ለማወቅ እስካሁን ካየሁዋቸው የተሻለ መንገድ ነው ብዬ የማምነው፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ጽሁፉችን ዝምብሎ ማንበብ ስልህ የአንተ ፍላጎት(interest) ያለበት አካባቢ አለ አደል፣ እኔ አሁን ለምሳሌ እግርኳስ ስለምወድ በእግርኳስ ዙሪያ የተጻፉ የኢንግሊዝኛ አንቀጾችን በፍቅር ስለማነባቸው የኢንግሊዝኛ ክህሎቴ በጣም አድጓል፣ ከምንም በፊት በግድ መጋት እንዳይሆንብህ ፍላጎትህን ለይ እና follow your interest. በተጨማሪ የኢንግሊዝኛ ፊልሞችን ያለ ትርጉም ዝምብለህ እያቸው፣ ከሰው ጋር በማህበራዊ ሚዲያ በኢንግሊዝኛ ኮምኒኬት ለማድረግ ሞክር ለአረፍተ ነገሮችህ ሳትጨነቅ፣ አደራህ በመጨረሻ ልልህ የሚፈልገው ነገር ብኖር አትጨናነቅ ሁሉንም ስታደርግ በፍቅርና በምርጫህ ይሁን።
Jul 22, 2022