guys pls be Ethiopian orthodox ena Catholic church mehakel yalewn leyunet be acheru asredugn pls guys
Jul 20, 2022በምንም አንገናኝም። ዶግማዊ ልዩነቶች፦ 1) ኦርቶዶክስ "ከሁለት አካል አንድ አካል፤ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ በተዋህዶ የከበረ ኢየሱስ ክርስቶስ" ሲባል፥ ካቶሊክ ዘንድ ደሞ "አንድ አካል፤ ሁለት ባሕርይ" ይባላል። 2) ኦርቶዶክስ ሠራጺ መንፈስ ቅዱስ የሚሠርጸው ከአብ ነው የሚል አስተምህሮ ስታስተምር፥ ካቶሊክ ደሞ ከ1054 ዓ.ም በኋላ ከወልድም ይሠርጻል የሚል አስተምህሮን ያስተምራሉ። 3) በኦርቶዶክስ አስተምህሮ የራስህን destiny እግዚአብሔርን በፍቃድህ ጣልቃ ካላስገባህበት በቀር የምትወስነው እራስህ ነው ስትል፥ ካቶሊክ ደሞ ከፈጣሪ ዘንድ አስቀድሞ ተጽፎልሃል የሚል እምነት አላቸው። ይህ አስተምህሮ ለማርቲን ሉተር ተቃውሞ the very first ምክንያቱ ነበር። ቀኖናዊ ልዩነት፦ 1) ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ አለቃ በኦርቶዶክስ የሀገሪቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲሆን የካቶሊክ ደሞ የሮማው ጳጳስ ነው። 2) የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ አካል(ገዢ) ቅዱስ ሲኖዶሱ(ጉባኤ ጳጳሳት) ሲሆን የካቶሊክ የበላይ ገዢ ራሱ የሮማው ጳጳስ ነው። ስናብራራው- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓትርያርኩ የፈለገውን የመሾም፣ የመሻር፣ የመወሰን እና የመደንገግ ሙሉ መብት የለውም፥ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ያለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሹማቸው፣ ሽረታቸው፣ ውሳኔያቸውና ድንጋጌያቸው አይጸናም። ባጠቃላይ ቤተክርስቲያን የምትገዛው በቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስቆጶሳት ስምምነት ነው። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደሞ የበላይ ገዢ የሮማው ጳጳስ እንደመሆኑ በስልጣኑ በሁሉም ላይ ነው። የፈለገውን የመሻር፣ የመሾም፣ የመደንገግ፣ የመወሰን ሥልጣን አለው። 3) የኦርቶዶክስ ፓትርያርክና ቅዱስ ስኖዶሱ ልኬታቸው ባላቸው አህጉረ ስብከት እንጂ የእህት አብያተ ክርስቲያናት ላይ ገዢ የመሆን ሥልጣን የላቸውም፥ ይህም ማለት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በግብጽም ሆነ በሶርያና በሌሎች አብያተክርስቲያናት ላይ ፍጹም ሥልጣን የላቸውም። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ግን እህት አብያተክርስቲያናት የለም፥ ሁሉም አብያተክርስቲያናት የሚተዳደሩት በሮማው ቤተክርስቲያን ሥር ነው። 4) በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ፓትርያርኩ እንደማንኛውም ሰው ሊሳሳት፣ ሊበድልና ትክክል ላይሆን ስለሚችል ለውሳኔው መካሪ፣ ካጠፋም ኃጥያቱን የሚናዘዝበት ንሰሐ አባት ሊኖረው ይገባል የሚል ትምህርት አለ። በካቶሊክ አስተምህሮ ደሞ የሮማው ፖፕ አይሳሳትም፥ ውሳኔው ድንጋጌው ቃላቱ ሁሉ የተቃኑና በቅዱስ ጴጥሮስ ኃይል የታገዘ ነው የሚል ትምህርት አላቸው። 5) የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመጀመርያ 3ቱ ጉባኤያትን (ጉባኤ ኒቅያ፣ ቁስጥንጥንያና ኤፌሶን) ብቻ ተቀብላ ከዛ በኋላ ያሉትን "የመናፍቃን ጉባኤ" ብላ ስትቀበል፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደሞ 21 ጉባኤያትን የዓለም ዓቀፍ ጉባኤያት አርጋ ትቀበላለች። 6) በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ንጹሕ ሆኖ ይገኝ እንጂ ማንኛውም መነኩሴ ለሥልጣነ ፓትርያርክ መታጨት ይችላል። እጩዎችን የማውጣትና የመመልመል ሥራ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት(የጳጳሳት) ብቻ ነው። በተለያየ ምክንያት፤ ማለትም በተገለጠላቸው ራእይ ወይም ደሞ በተደረገው ጥልቅ ምርመራ ከነዛ ሰዎች ሁሉ አንድ ሰው ብቻ ብቁ ሆኖ ከተገኘ ያ ሰው ለፓትርያርክነት ይታጫል። ግን ደሞ ለዛ ሥልጣን ብቁ ሆነው የተገኙ ከሁለት በላይ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም መነኮሳት ከተገኙ ታላቅ የጸሎት መርሐ ግብር ከተደረገ በኋላ ከጸሎቱ መኻል በእድሜው ትንሽ የሆነው ብላቴና ይጠራና ዐይኑ በጨርቅ ታስሮ ዕጣ እንዲያነሳ ይደረጋል፥ ህጻኑ ያነሳው መነኩሴ ወይም ጳጳስ የቤተክርስቲያኒቱ አዲስ ፓትርያርክ ተደርጎ ይመረጣል፥ በሚመጣው እሁድ ይቀባል። (ማሳሰቢያ- ፩- የኦርቶዶክስ ጳጳሳትም ሆነ ፓትርያርክ የግድ ደናግላን እና መነኮሳት መሆን አለባቸው። -፪- ፓትርያርክ ለመደረግ የሚመከረው እድሜን ከ50 በላይ ቢሆንም እንደ ግዴታ አይቀመጥም። -፫- አእምሮውና አካሉ ግን ሙሉና ጤነኛ መሆን አለበት። የአእምሮ ታማሚ፣ ዐይነ ስውር፣ የማይሰማ፣ 2ቱን እጅና እግር የሌለው መሾም አይችልም) ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ደሞ የሮማው ጳጳስ(ፖፕ) መሆን የሚችሉትም ሆነ መምረጥ የሚችሉት ካርዲናሎች ብቻ ናቸው፥ አልፎ አልፎ ግን ጥቂት ጳጳሳት የመመረጥ እድል ሊኖራቸው ይችላል። አዲስ ፖፕ ሊመረጥ ሲል ካርዲናሎቹ በትልቅ አዳራሽ ይሰበሰቡና በሩ ተዘግቶባቸው እዛ ውስጥ ምስጢራዊ ውይይት ያደርጋሉ። ማን መመረጥ እንደሚገባም እዛ ውስጥ በወረቀት ይጽፉና ተመራጩ ፖፕን ይመርጣሉ። አዲስ ፖፕ መመረጡን ለመግለጽም የምርጫ ወረቀቱን በነጭ ጪስ ማቅለሚያ አድርገው ያቃጥሉትና ውጭ ላለው ህዝብ ያሳስባሉ። በነጋታው አዲሱ ፖፕ ለህዝቡ ይፋ ይሆናል። (ማሳሰቢያ-፩- ፖፕ ለመሆን ምንኩስናና ድንግልና ግዴታ አይደለም።-፪- ፖፕ ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ ግዴታ ከ80 ዓመት በታች መሆን አለባቸው። -፫- ልክ እንደ ኦርቶዶክሱ ሙሉ አካላዊና እእምሮ ጤነኝነት ሊኖረው ይገባል) በተጨማሪ- የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ሲሰየም ጳጳስ ከነበረ በስመ ጵጵስናው፥ መነኩሴ ከነበረ ደሞ ሲኖዶሱ ባወጣለት ስም ይሰየማል። በካቶሊክ ደሞ አዲሱ ፖፕ "ስምህ ማን ይሁንልህ?" ተብሎ ይጠየቃል። እሱም የጠራው ስም Papal ስሙ ይሆንለታል።
Jul 21, 2022