ሰላም ቤተሰብ እስቲ በደንብ ስለ መለኮት የሚያስረዳኝ ካለ እባካችሁ ኦርቶዶክሶች ተባበሩኝ
Jul 20, 2022እኛ #ኦርቶዶክሶች መለኮት ስንል #ግዛት #መንግስት #ሥልጣን #ባህርያዊ_አምላክነት #ፈጣሪነት #አምላክነት እያልን ነው። መለኮት አንድ ሲሆን በሶስት አካል ይገለጻል። አብ የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው። ወልድ የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው መንፈስቅዱስ የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው። በመለኮት አንድነት አላቸው። #መለኮት እሳት ነው ይኽም እሳት አስገኚ እንጂ የተገኘ አይደለም። ምድራዊ እሳት ቢበላ ቢያቃጥል ስጋን ነው ረቂቅ እሳት ቢበላ ቢያቃጥል ነፍስን ነው መለኮታዊ እሳት ግን እሳትን የሚበላ እሳት ነው። መለኮት በዚኽ አለ በዚያ የለም የሚሰኝ አይደለም በኹሉ የመላ እንጂ። ለመለኮት ፊት እና ጀርባ ግራና ቀኝ የለም።መለኮት ጥልቀቱ እስከ በርባኖስ ቁመቱ እስከ አርያም ዳሩ እስከ ናጌብ ስፋቱ እስከ አድማስ ተብሎ አይወሰንለትም። እሱ መለኮት ሁሉን ወስኗል እንጂ። (ውይ እምዬ ማርያም😍😍😭😭 እናቴ ምን ልሁንልሽ የማይወሰን ወስነሽ በበረሀ መሰደድሽ) መለኮት. . . . ጠይቅ እስኪ
Jul 20, 2022