ሰላም ቤተሰብ ይሄ ጥያቄ ሁለቱም ፆታ ይመለከታል !! የፍቅር ወይም የትዳር አጋራችንን ስንመርጥ ዋና የሚባለው መስፈርት ምን መሆን አለበት ብላችሁ ታስባላችሁ?ገንዘብ,መኪና,ቤት, መልክ ,የሰውነት አቋም ወይም ቅርፅ,ወይስ ደግሞ ከቁሳቁስ ግብስብስ ነገሮች ውጪ ወጥታችሁ የዛን ሰው ንፁህ ፍቅር , ንፁህ ማንነት እና ስብእናውን በገንዘብ ሊለካ የማይችል ሰውነቱን ...መስፈርቶች የትኞቹ ቢሆኑ የሁለቱ ሰዎች ፍቅር እስከመጨረሻው ሊቀጥል ይችላል??እስኪ ሀሳብ ስጡበት 🙏🙏🙏
Jul 19, 2022እንላለን እንጂ ፍቅር ምንም መስፈርት የለውም። ፍቅር ከሁሉም ነገር ለየት የሚያደርገው ነገር የምታስቀምጣቸውን መስፈርቶች ሁሉ ጥሶ ያሸንፍሃል። ከዛ በኋላ ለሴት ብለህ አስቀምጠህ የነበርከውን መስፈርት እነሱም ትተህ እራስህን መለካት ትጀምራለህ፥ በዛው ሂደት "አልመጥናት፣ ትበዛብኝ ትሁን" ወደ ሚለው ትመጣለህ እንጂ ለመስፈርትህ ብለህ ፍቅርን ማሸነፍ አትችልም። ፍቅርን ማሸነፍ የሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው። ባሁን ሰዓት እኔ መስፈርት ብዬ ማስቀመጥ የምችለው ሀይማኖቴን ብቻ ነው። ምንም ያህል ይሁን የሰው ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊበልጥ አይገባም።
Jul 19, 2022