ጥያቄ ለ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች 1- ሰንበት እሁድ ነው ወይስ ቅዳሜ ወይስ ሁለቱም? 2- በ በዓላት ቀን ስራ አይሰራም ለምሳሌ ልብስ አይታጠብም ለምን እና ደሞ የዓመት በዓል ጊዜ ብቻ ነው ወይስ በየወሩ ? እባካችሁ በቅንነት መልሱልኝ
Jul 18, 2022በቤተ ኤዎስጣጤዎስና በቤተ ተክለሃይማኖት ዘንድ የነበረ ክርክር ነበር። ኋላ በ2ሰንበታት ተወስኗል። #ፍካሬ ሃይማኖት ተመልከት። ከዚ ባሻገር ሁለቱም ሰንበታት ስለመሆናቸው ምስክር ላምጣ ቀዳሚት ሰንበት ይኽችውም ቅዳሜ ናት ከስራ ሁሉ ያረፈባት ይኽች ዕለት ዳግመኛ በሐዲስ ኪዳንም አርብ ተሰቅሎ ቅዳሜ በመቀብር አድሮ አርፎባታል። ሕግና ነቢያትን ሊያጸና የመጣ አምላክ በብሉይ እንድትከበር አዝዞ በሐዲስ አልሻራትም ቃሉ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላልና። እሁድ ከዕለታት የከበረች ፍጥረታትን የጀመረባት ነገረ ድኅነትን በመጸነስ የጀመረባት የተነሳባት ዳግም የሚመጣባት ዓለምም አልፎ የምትሮን የከበረች ዕለት። 2ሰንበታት። በበዓላት አዎ ስራ ይሰራ ዘንድ አልተፈቀደም። ምን አይነት ስራ? ተግባረ ስጋ። በሰንበት የሚሰራው ተግባረ ነፍስ ነው። ምሳሌ ልብስ ማጠብ ብለሀል የራስህን ልብስ ታጥብ ዘንድ አልተፈቀደልኽም የደሀ ልብስ ታጥብ እንጂ። በየወሩ በ12 በ21 በ29 በሰንበታት ተግባረ ስጋ አልተፈቀደም። ለስጋ አድሮ መሸፋፈን ጥሩ አይደለም። ድርሳነ ሰንበት ድርሳነ ሚካኤል ተዓምረ ማርያም ይመስክሩ። ድርሳነ ሚካኤል ሰንበትን በሚሽሩ 3መቅሰፍታት ታዝዘዋል #እርስ በርስ እልቂት #ርሀብ #ቸነፈር ይኽ በሀገራችን እየሆነ ያለው ነው የመአቱ አንዱ ምክንያት ሰንበትን እንደ ሀገር ሙልጭ አድርገን ሽረናልና ቁርጥምጥም አድርግን በልተናቸዋል። የሰንበት አምላክ ከጥንትም ተናግሪአለው አሁንም እጮኽልሻለው #ሰንበታት አክብሩ #በዓላት አክብሩ። መንግስት በግድ እጃችሁን ጠምዝዞ ለእንጀራ እንድትሽሩ አድርጓል #እንቢ በሉ። ኦርቶዶክሳዊያን የመንግስት መዋቅርን ተመልከቱ ሀይማኖታችሁን የሚጋፋ ነው። ራሳችሁን አድኑ ለሆዳችሁ አትደሩ። ያኔ ምን ያክል ዓለም ቦታ እንዳሳጣችሁ ትረዳላችሁ። እርስ በርስ ተረዳዱ ተደራጁ በዓላት የምታከብሩበት የራሳችሁን ስራ ስሩ። እውነቱ ይኽ ነው።
Jul 18, 2022