Aselamu aleykum Seid yaseen akababi elalew quran bet mereja magegnet felge nbr ena mtawku kehone w Weym all kutrachewn
Jul 14, 2022ስለ ሒፍዝ ቦታ በተደጋጋሚ ለምትጠይቁኝ‼ ============================= «ማስታወቂያ 💥ዛዱል-መዓድ የቁርኣን ሒፍዝና የተርቢያ ማዕከል ለመጪው ዓመት (1444ዓ.ሂ/2015ዓ.ል) የቀን ሙሉ ተመላላሽ የቁርኣን ሒፍዝና ተያያዥ ትምህርቶች የሚሰጥበት ፕሮግራም ምዝገባ ጀምሯል። ✨መስፈርቶች✨ 1⃣ተመዝጋቢዎች እድሜያቸው ከ13 በላይ፣ከ21 በታች መሆን አለበት። 2⃣ቁርኣን በማየት በተጅዊድ ያኸተመ/ች መሆን አለበ/ባት። 3⃣ የሒፍዝ ፕሮግራሙ የሁለት ዓመት ሲሆን ቀድሞ የተወሰኑ ጁዝኦችን የሐፈዘ ወይም ፈጣን የሒፍዝ አቅምና ችሎታ ያለው ተማሪ በአንድ ዓመት አጠናቆ መውጣት ይችላል። 4⃣ ፕሮግራሙ (ትምህርቱ) የሚጀመረው ሙሐረም (መስከረም መግቢያ) ላይ ይሆናል። ⚡️ፕሮግራሙ ለወንዶችም ለሴቶችም ነው። 💥ይህ በእንዲህ እንዳለ በዘንድሮ (1443ዓሂ) ክረምት በተመላላሽ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:30 እና ከአስር እስከ መግሪብ ባለው ሰዓት ታዳጊ ወንድ ተማሪዎችን፤ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:30 ባለው ጊዜ ደግሞ ታዳጊ ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ከነባር የሒፍዝ ተማሪዎች ጋር ማስተማር ይፈልጋል። ✨መስፈርቶች✨ ✅ ወንዶች እድሜያቸው ከ10 ዓመት በላይ መሆን አለበት። ✅ የሴቶች ከ8 እስከ 16 ባለው መሆን አለበት። 🔅ለሁለቱም ፕሮግራሞች ማስመዝገብና እድሉን መጠቀም ለምትፈልጉ 🗓 የምዝገባ ቀን:- የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ (ሐምሌ11/12) ⏰ የምዝገባ ሰዓት :- ከዙህር እስከ መግሪብ 📌አድራሻ :- ፉሪ በድር መስጂድ አካባቢ ⚠️ማሳሰብያ⚠️ 📛 ለየት ያለና ተመክሮ የማይታረም ሌሎችን ሊበክል የሚችል መጥፎ ፀባይ ያለበትን ተማሪ አንቀበልም፤ ከተመዘገበ በኋላም በእንዲህ ዓይነት ባህሪው ሊመለስ ይችላል። ⛔️ያለን ቦታ ውስን ከመሆኑ አንፃር ቅድሚያ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ ስለሆነ ፈጥነው ያስመግዝቡ። ☎️ለበለጠ መረጃ +251972344383 (ለወንዶች) +251947346787 (ለሴቶች)» ©: ዛዱል መዓድ
Jul 14, 2022