እኔ ምለው ሃብታም ለመሆን ፀሎት ነው melfat ሚያስፈልገው አንዳንዴ ሰዎች ግስጥብለው ያለ ሥራ ከነ ጭምር ሃብታም አርገን ብለን እን ፀልያለን ግን ጠብ ያለ ንግር የለም እኔ በበኩሌ ምንም ንግር ፀልየ teskatolign አያውቅም ምንድነው ችግሩ 🤔
Jul 13, 2022አንድ የዋህ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ እንዲኽ የሚል ቃልን አገኘ "የሰማይ አዕዋፋት ተመልከቱ አይዘሩም አያጭዱም ጎተራም የላቸውም የሰማይ አባታቸው ይመግባቸዋል" ይኽን ቃል በመያዝ ይኽ የዋህ ሰው የምግቤ ነገር ከተያዘልኝማ ስለምን በዋሻ ውስጥ በጸሎት ተወስኜ አልኖርም በማለት ወደ ዋሻ አቀና። ከአንዲት ዋሻም እንደደረሰ በዛው ተባሕቶ ለመያዝ ከዋሻዋ ገባ ቀኑን በጸሎት ዋለ አደረም የወረደ መና ግን አልነበረም። ሁለተኛ ቀንም በተመሳሳይ መልኩ በጸሎት ሲተጋ ዋለ አደረ የወረደ መና አሁንም አልነበረመወ 3ተኛ ቀን 4ተኛ ቀንን እያሳለፈ ሲመጣ ድካም ተሰማው ለጸሎት መትጋት እስኪሳነው ኃይልን አጣ የሰውየውን የልብ የዋኽነት የተመለከተ እግዚአብሔር መልአኩን ላከለት. .መልአኩም ለዚኽ የዋህ ሰው በመገለጥ ስለምን የምትበላውን ለመፈለግ ከዋሻ አትወጣም ሲል ጠየቀወው ሰውየውም መጽሐፍ "የሰማይ አዕዋፋት ተመልከቱ አይዘሩም አያጭዱም ጎተራም የላቸውም የሰማይ አባታቸው ይመግባቸዋል" ይልም አይደል ብሎ ይመልስለታል ይኽን ግዜ መልአኩ የሰማይ ወፎች አይዘሩም አያጭዱም ተባለ እንጂ አይበሩም ተባለ ? ሲል ለየዋህነቱ ምላሽ በመስጠት ኃይልንም አስታጠቀው። ለምን ይመስልሀል "ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ሰፋ" የተባለው እና ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ የሚሰፋው ? አንድም ከኃልዮ ኃጢአት ራሱን ሊጠብቅ ቢሆንም። ስለዚኽ እየሰሩ መጸለይ እንጂ "ተቀምጦ ማንጋጠጥ በእግዜር ማልመጥ" መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። ምንም ነገር ጸልዬ ለምን ጸሎቴ አልተሰማም ላልከው ግን እግዚአብሔር በባህሪው አለመስማት አይችልም አንተ ምላሹን አልተረዳኽ ይሆናል እንጂ። ጸሎት ስሙር እንዲሆን ግን ልብና አንደበት መስማማት ይኖርባቸዋል። የምትለምኑትን አታውዉቁም ያለ ጌታ አስቀድማችኹ ጽድቁን እና መንግስቱን እሹ ብሏልና ከምን መጀመር እንዳለብኽ ለይ። #ንስሀ_ግቡ።
Jul 14, 2022