Selam sewoch Tyakrye ene ahun ke 5 wer mnamn behuwala 17 amet yhonegnal..... ena footballer mehon new mfelgewna ene trainiing serche alakm gin betam yekuwas interestu ena flagotu alegn ena tesetowm alegn seferm echawetalew ena jelesoch lemn training ajemrm ylugnal... ena ahun training lemejemer edmeye yehede ymesluwachuhal? Ena bjemrm likebd aychlm?... ena demo debrezeyt negn
Jul 11, 2022ምንም ቢፈጠር ተስፋ እንዳትቆርጥ! እኔም እንዳንተው የ 17 አመት ልጅ ሳለሁ ከባድ የሆነ የኳስ እና የሩጫ ፍቅር ነበረኝ። በወላጆቼ ግፊት ምክንያት ትምህርቴ ላይ ፀንቼ ቀረሁ እንጂ የራሴን ወደፊት የማየው በእግር ኳስ ነበር። የዛኔም እንዳንተው የረፈደብኝ ይመስለኝ ነበር። አስበው እስኪ.. ከዚህ በኋላ ለ5 አመታት ያህል ያለ መወላወል ራስህ ላይ ብትሰራ! ያለ ስንፍና ለ5 አመት ያህል በምትወደው ኳስ 'ትሬይኒንግ'/ልምምድ ብታደርግ 22 አመት ሲሞላህ ራስህን የት ልታገኝ እንደምትችል። እመነኝ ለሀገራችን ከባዱ ሰው ነው የምትሆነው። 5+5=10 አመት ብትለፋ ደግሞ የ27 አመት ወጣት ሆነህ ኳስን እንደፈለግክ ማድረግ ስትችልስ? ከሀገርህም ወጥተህ የተሻለ 'ክለብ' ስትጫወትስ? የራስህን፣ የቤተሰብህንና የሀገርህን ስም ስታስጠራስ? ህልምህን ለማሳካት ማንንም እንዳትጠብቅ! ወላ ወላጅ ወላ ወዳጅ እንዳትሰማ! የ16 አመት ልጅ ሳለሁ አንድ እንደ ጓደኛ የምቀርበው ወዳጅ ዶክተር "ከዚህ በኋላማ አንተ ኳስ ተጫዋች መሆን አትችልም!" ይለኝ ነበር። ስራ ምናምን ጨርሶ ቤቱ ሳይገባ እኔ ጋ እየመጣ ይቀመጥና ህልሜን እንድቀይር ይወተውተኝ ነበር። ዶክተር የነገረንን ሁሉ የማመን ችግር ያለብን ኢትዮጵያውያኖች አይደለን.. አመንኩት። ለካ ከጊዜ በኋላ ሲገባኝ ዶክተሩ መድረስ የፈለገበት የህክምና ደረጃ ነበር። እድሜው በመግፋቱ እና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ያን ህልሙን ባለማሳካቱ እኔን እዛ የህክምና ደረጃ ላይ ሊያየኝ ይመኝ ስለነበር ነው ለኳስ ያለኝን ፍላጎት የገደለብኝ። እሱ ለክፋት አይደለም ተስፋ ያስቆረጠኝ። በህክምናው ዘርፍ ለሀገሬ የተሻለ እንዳበረክት ስለተመኘልኝ ነበር። የሆነው ሆኖ አንተም እንዲህ የህልምህን ፍላጎት እና የራስህን አቅም የሚገድሉ ብዙ ወዳጅም ጠላትም ስለሚኖርብህ ማንንም እንዳትሰማ! ታመሰግነኛለህ። አንድ ቀንም በቲቪ ወጥተህ "የማላውቀው ሰው መክሮኝ ለዚህ በቃሁ" ብለህ ስታመሰግነኝ እመለከትህ ይሆናል። የኔን ህልም ባንተ እንደማይ ተስፋ አደርጋለሁ። በርታ!
Jul 12, 2022