ሰላም አዲስ ሙሽራ ነኝ እና ከባለቤቴ ጋር በጣም ተዋደንና ተፋቅረን ነው የተጋባነው ነገር ግን እኔ በsex ባለቤቴን ማስደሰት አልቻልኩም ምክንያቱም ስንጋባ እኔ ድንግል ነኝ እናም በግንኙነት ሰአት በጣም ያመኛል እና ሲያመኝም ባለቤቴ ለኔ እያዘነ ስሜቱ ካቅሙ በላይ ቢሆንበትም ሲያመኝ ይተወኛል እስካሁንም ትክክለኛ ግንኙነት ማድረግ አልቻልንም ህመሙን ለመቀነስ ብዙ መንገዶችን ብንሞክርም በግንኙነት መደሰት አልቻልንም መፍትሄ ከናንተ አይጠፋም ምከሩኝ
Jul 10, 2022እንኳን እግዚአብሔር ለጋብቻ አበቃሽ ሳልልሽ አላልፍም። እግዚአብሔር ትዳራችሁን ይጠብቅላችሁ፥ መልካም ፍሬ ይስጣቹ። ወደ ጉዳዩ ከመምጣታችን በፊት 18 በታች የሆኑት ባያነቡት ይመከራል። እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች በመጀመርያ ግንኙነትም ብቻ ሳይሆን በቆየ ትዳር ውስጥ ራሱ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች ናቸው። ክብረንጽህናሽን ጠብቀሽ ያገባሽ እና ለግንኙነት መጀመርያ እንደመሆንሽ ለሁለት ምክንያት ሲባል ላይሳኩ ይችላሉ። የመጀመርያው፥ አብዛኞቹ በድንግልና የኖሩት ሴቶች በማኅጸናቸው ጫፍ ላይ ማኅተመ ማኅጸን(hymen) አላቸውና ብዙ ጊዜ በግንኙነት ሰዓት ላይ የሚበጠስ ወይም tear down የሚደረግ ነው። እናም ለብዙ ሴቶች የህመም ስሜት ይሰጣል፥ በተለይም ማእተማቸው በጣም የተሸፈነ ከሆነ ግንኙነት መፈጸም በጣም ህመም የተሞላ ያደርገዋል። ለዚ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው ~አንደኛው ግንኙነት ራሱን መፈጸም ነው፤ ግን ደሞ በማኅበረሰብ ውስጥ ስለሚኖር ድምጽ ከመኝታ መውጣት የለበትም። ግን የተሻለ መፍትሄ ይህ እንደመሆኑ ሁኔታውን መጋፈጥ ግድ ሊሆን ይችላል። እንደጤና ባለሙያዎች ምክር ህመምን ለማስታገዝ ከግንኙነት 1 ሰዓት በፊት Ibuprofen መጠቀም ይመከራል። ሌሎች መድኀኒት ግን አይቻልም። ~ ሁለተኛው ደሞ፤ በሰርጀሪ ነው። እሱ ከሁሉም ህመም የሌለው ቀላሉ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የትዳር አጋሮች በጤና ባለሙያዎች ላይ እምነት አይጥሉም። ሁለተኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ደሞ Sex trauma ነው። ይህ በመጀመርያ ሙከራም ሆነ ባደረ ትዳር ውስጥም ሊከሰት የሚችል ነው። ይህም በጤና እክልም ሆነ Sex በመፍራት የሚመጣ የታችኛውን አካል መቆጣጠር አለመቻል ነው። ይህ ለግንኙነት አዲስ በሆኑት ላይ ሊከሰት ይችላል። ምክንያትም ሊሆን የሚችለው ደሞ ራቁታቸውን ከመግለጥ ጀምሮ መዳራቱ የሚያሳፍራቸው እንደመሆኑ እካላቸውን በነቂስ ስለሚጠብቁ፥ ከዚ በፊትም ፈጽሞ የሚያውቁ ከሆነም ደሞ በባለፈው ላይ traumatized ስለሆኑ፣ ወይም ደሞ የማኅጸን ድርቀት ስላለባቸው እና የመሳሰሉት ምክንያት ይሆናሉ። ይህም ሲሆን የማኅጸን በራቸው መከፈት ባለበት ልክ ስለማይከፈት በግንኙነት ሰዓት ላይ የሚፈጠረው friction ህመም ይፈጥርባቸዋል፥ ከዛም አልፎ አንዳንድ ጊዜ የወንዱ ብልት በሴቷ ማህጸን ውስጥ ተነክሶ(ተይዞ) የሚቀርበት ጊዜ አለ። ይህ ሁሉ ሊሆን ይችላል ግን ለዚ ሁሉ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው መደናገጥ ሳይሆን ምንም እንዳልተፈጠረ በመረጋጋት መዳራት (Warming up) ነው። እንጂ መደናገጥ ትክክል አይሆንም። ባጠቃላይ፥ ጾታዊ ግንኙነት ውስጥ በተለይ ለሴት በጣም አስፈላጊው ነገር Oxytocin ሆርሞን ነው፥ ይህ የፍቅር ሆርሞን በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሰውን፣ ባለቤትን፣ ልጅን ስንወድ በፍቅራችን መጠን የሚመነጭ ሆርሞን ነው። ይህ ሆርሞን በብዛት በመነጨ ቁጥር የማኅጸን ጡንቻዎች relax እንዲያረጉና ለጾታዊ ግንኙነት/ለወሊድ ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ስለዚህ ይህ ሆርሞን በግንኙነት ሰዓት ላይ በብዛት እንዲመነጭ ከተፈለገ it needs more foreplay። I hope it helps. ያው ባለትዳር እንደመሆንሽ አልጋችሁም ቅዱስ ነው በሚል እንጂ ሌላ ሰው ቢሆን ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆንም ነበር። ፈጣሪ ትዳራችሁን ይባርክ።
Jul 11, 2022