Selam nachihu everyone, Can someone please give me some explanation on metaverse and how it works? Thanks in advance.
Jul 08, 2022በቅድሚያ እነዚህን ካላየሀቸው እያቸው ካየሀቸው የማብራራልህ ይገባሀል በደንብ:: 1. ሬዲ ፕለየር ዋን(የ2017ፊልም ነው) 2. ሰከንድ ላይፍ(የኦንላይን ጌም ነው) 3. VR/AR(የቴክኖሎጂ አይነቶች ናቸው) 4. NFT(የመገበያያ ከረንሲ ነው) እነዚህን በደንብ ከተረዳህ እንቀጥል ካልተረዳህ ትንሽ ገርባቸው ጎግል ላይ ግባና ፊልሙንም ትሬለሩን ካየኸው በቂ ነው:: ወደጥያቄህ ስንመጣ ሜታቨርስ ማለት ልክ እንደ ዩኒቨርሶችን የራሱ የሆነ በ3ዳይሜንሽን (3D) ቴክኖሎጂ ተገጣጥሞ በኦንላይን እንደጌም የሚገኝ አንድ ትልቅ ዩኒቨርስ ማለት ነው(ሁሉም ነገር የሚከወነው በምናባዊ/አኒሜሽን መልክ ነው) ለምሳሌ ከላይ ከጠቀስኩል አንዱ የሆነው ሰከንድ ላይፍ የተሰኘውን የኦንላይን ጌም ካየኸው የራሱ የሆነ አለም አለው ልክ አሁን እንዳለንበት የተገነባ በጌም መልክ ለምሳሌ ስትገባ አንተ ቦታህን ታስመዘግባለህ ፆታ እድሜ ምትወደውን ነገር ምናምን ከዛ ያንን ይቀበልህና ራሱን የሚመስል ይፈጥርልሀል በ3ዲ ከዛ አንተ የፈለክበት ሀገር ከኢትዮጲያ ተነስተህ ቴሌፓርት እያደረክ ከሰዎች ጋር ታወራለህ ትዝናናለህ እቃ ትገዛለህ ትበላለህ ትነዳለህ መጥፎ ነገሮችን ታደርጋለህ እውነታው አለም ላይ ምታደርገውን በጌም መልክ ትተገብረዋለህ ሁለት አይነት ካራክተሮች አሉ እዛ ጌም ላይ NPC እና PC እነዚህ ካራክተሮች አንዱ አንተን ወክሎ የሚጫወተው ሲሆን ሌላኞቹ ደግሞ ኮምፒውተሩ ባዘዛቸው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ስለዚህ ልክ እንዳንተ ሌሎች ሰዎች በተመሳሳይ ሰአት የሚያንቀሳቅሷቸው ይኖራሉ ማለት ነው(ይህ አሁን ብዙ ጌሞች እየተገበሩት ይገኛሉ መነሻው ግን ሰከንድ ላይፍ ያልኩህ ኦንላይን ጌም ነበር) እና ምን አገናኘው ከጠየኩት ጋር ካልከኝ ሜታ ቨርስ ማለት አሁን ከላይ የገለፅኩልህን ወደ ሪያሊቲ መጠቀሚያነት ማምጣት ማለት ነው:: እንዴት እናምጣው ሲባል በቅድሚያ ሪል ማስመሰል ያስፈልጋል ለዚህ ደግሞ VR/AR ስራቸውን ይወጣሉ ምንነታቸው ካላወክ ጎግል አድርጋቸው:: ከዛ እንዴት ወደ ጥቅም እንቀይረው ሲባል NFT/ክሪፕቶ ከረንሲ ለዚህ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ :: ስለ ሁለቱም ካልገባህ አሁንም ጎግል አድርግ ምክንያቱም ራሳቸውን የቻሉ ትልልቅ ቶፒኮች ናቸው::አሁን ሰዉ ተገኝቷል /ገንዘብ መገበያያው ተገኝቷል እውነት እንዲመስል ማድረግ ተችሏል ምን ቀረን የሚሸመቱት ነገሮች ቀሩን ማለት አይደል:: ለዛ ደግሞ ፌስቡክ/ናይኪ/ቴስላ...ብዙ ድርጅቶች መቀላቀልና የየራሳቸውን ቨርቿል ሱቆች እና ምርቶችን መገንባት ጀምረዋል(ማን-ሲቲ ለምሳሌ ትልቅ ስታዲየም ገንብቶ ክፍት ሊያደርግ እየጠበቀ ነው ለተመልካች) ስለዚህ ስንጠቀልለው ቤትህ ደቅ ብለህ VRህን አጥልቀህ NFTህን ከፍለህ የማን ሲቲን ጨዋታ መታደም ትችላለህ ማለት ነው ስታዲየም ውስጥ ያለህ እየመሰለህ:: በደንብ እንድትረዳው Ready Player One ሚለውን ፊልም በደንብ እየው ይገለጥልሀል ኮንሴፕቱ እና መጪው ትውልድ ምን እንደሚመስል::
Jul 09, 2022