እባካችሁ እስኪ ንገሩኝ🙏 አሁን 10ኛ ክፍል ተምሬ ጨረስኩ እና ከ kg ጀምሮ እስከ 9ኛ ክፍል የግል ነበር የተማርኩት ግን አሁን 10ን የመንግስት ተማርኩ ውጤቴም ትንሽ ዝቅ አለ የመንግስት ላይ፤እናም የመንግስት መማሬ 12ኛ ክፍል ላይ ተጽእኖ ካሳደረብኝ ብዬ ፈራሁ እናንተ ምን ትላላችሁ የመንግስት ልቀጥል ወይስ ወደ ግል ልመልስ😥🙏
Jul 04, 2022የግል ት/ቤት መማር በጣም dependent እንድትሆን ያረግሀል ማለትም ነገሮችን ሁሉ የምታደርገው የምታጠናው የምታነበው ምናምን ት/ቤቱ እና መምህራንህ የተሻለ ቁጥጥርና ክትትል ስለሚያደርጉ ነው። ላይመስልህ ይችላል ግን ነው። የመንግስት ት/ቤት ግን ራስህን በራስህ አስተምረህ የምትወጣበት ቤት ነው መምህራን ስላንተ መማር አለመማር ደንታ የላቸውም። ራስህን አጠንክረህ ጎበዝ ሆነህ የምታልፈው እዚህ ስትሆን ነው። 12ብቻ አይደለም ዩኒቨርስቲ ስትገባም እንዲሁ ደንታቢስ መምህራን ነው የሚገጥሙህ ስለዚህ ከወዲሁ ራስህን አስተካክል አጀግነው። ታድያ የተለያየ የመንግስት ወይም የግል ት/ቤት በተለይ የግል ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር connection ፍጠር networkህን አስፋ ምክንያቱም እነርሱ ጋር የተሻለ ማቴሪያል፣ ጥያቄዎች፣ notes፣ የመጽሐፍት ጥቆማዎች ስለማይጠፉ። በተረፈ ፈጣሪ ይርዳህ🙏 Good Luck!
Jul 04, 2022