ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ዛሬ አንድ ነገር ላስቸግርራችሁ አኔ ምኖረው ከ አያቶቼ ጋር ነው እና ያው አክስቶቼ እና አጎቶች ያግዙናል እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው አሁን ላይ እኔ የ 12'ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ማለትም ተፈታኝ ነኝ እና እቤት መጀመሪያ አካባቢ ዉጤት እንዲመጣ ይፈልጉ ነበር አሁን ላይ ግን ሌሎች ልጆች ውጤት ከቀረባቸው በሁአላ የኔ ውጤት መምጣት ዓለመምጣት ሚያሳስባቸው አይመስለኝም እኔ ደግሞ ውጤቱን እፍልገዋለው ምክንያቱም እኔ የራሴ አላማ አለኝ ችግሩ ምንድነው አሁን ውጤት ከመጣ በሁአላ ግቢ ሚልኩኝ አይመስለኝም ይሄ ደግሞ እኔን ከማንበብ እያገደኝ ነው እነሱ ካሉ ደግሞ አሉ ነው ከትእዛዛቸው መውጣት አልችልም እና ምን ላደርግ እባካችሁ እርዱኝ ምን ላድርግ በጣም ጨቆኛል 😔 ገንዘብ ምናምን አጎት እና አክስቶቼ ናቸው ሚያግዙን 😔😔 አመሰግናለው 🙏🏽🙏🏽🙏🏽
Jul 03, 2022መጀመመሪያ ፆታ ሴት ወይም ወንድ መሆንህን/ሽን አላወኩም። ቀለል ብሎኝ እንዳወራ በወንድ ወስጃለው። ሴት ከሆንሽ ይቅርታ። እና ደሞ ከምንም በላይ ዓላማ ስላለህ ደስ ይላል፤ምክንያቱም ብዙዎቻችን ያለን ቢመስለንም አናቀውም። እና ከ12 ዓመት በላይ ለፍተህ አሁን ላይ በተወሠኑ ችግሮች ምክንያት ይሄ ሁሉ ድካም ከንቱ እንዲሆን ማረግ አይገባም። እነሱ ነገ ያንተን ህይወት ሊኖሩ አይችሉምና፤ ችላ አሉኝ ወይም እንዳነብ ተገቢውን ጊዜ አልሠጡኝም ብለህ ካለህበት ቅንጣት እንኳን ፈቀቅ እንዳትል። ሁሉም ያልፋል። እስከዛ ጠንክር ያለህን ሠዓት ትንሽም ቢሆን ተጠቀምባት፤ የሆኘ ሠዓት ይሄም ጊዜ ያልፍና፥ ትልቅ ቁም ነገር ላይ እንደምደርስ አምናለው። ፈጣሪ ካንተ ጋር ይሁን። አሜን
Jul 04, 2022