Hello everyone እናቴ በbrain atrophy በሚባል በሽታ ታማለች እና በሽታው በቀን በቀን እየባሰ የሚሄድ በሽታ ነው ...በቃ እንደሰው normal አይደለችም በአፏ ለመናገር ስትሞክር አንደበቷን ይይዛታል...አንድ ቦታ ላይ ብቻ ፍጥጥ አርጋ ነው የምታየው...ምግብ በእጇ መመገብ አትችልም...ተቀምጣም ተኝታም እራሷን ስለሚያዞራት አትንቀሳቀስም...በቃ በአጠቃላይ normal የሆነ ሰው የሚያደርገውን ማድረግ አትችልም...አባቴም በተመሳሳይ በሽታ ለ7 አመታት ታሞ ከሞተ 3 አመት ሆነው ...በቃ ቤታችን ውስጥ ደስታ ከጠፋ 10 አመት ሆነን ሁሌ ጭንቀት ነው እናቴም ያለችበትን ሁኔታ ስታይ ሁሌም እንዳለቀሰች ነው...እህቶቼ እሷን ለማስታመም ብለው የራሳቸውን ህይወት አልመሰረቱም እኔም እዚሁ AAU ተማሪ ነኝ ግን በዚሁ ምክንያት ትምህርት ምንም አልገባ አለኝ ላጠና ወይም በትኩረት ለመማር ሳስብ ይሄ ጉዳይ ያስጨንቀኛል ውጤቴም በየሴሚስተሩ እየወረደ ነው ...ብቻ በአጠቃላይ የምድር ህይወት ገሀነም ነው የሆነብን...ደስታ ባለው ቤተሰብ ሁሌ እንደቀናሁ ነው...ፀበል ያልሞከርነው የለም ምንም አዲስ ነገር የለም...i kw እንዳበዛሁት ግን የምተነፍስበት ስላጣሁ ነው atleast ደና ዘመድ እንኳን የለንም...እስኪ ምን እናድርግ?????
Jun 25, 2022እግዚአብሔር ለታመሙት እናትህ ጤናና እድሜ ይስጥልህ ። ጠበል መጠመቃቸው መልካም ሆኖ ሳለ ድኅነት ቅጽበታዊ አይደለምና በእምነትና በተስፋ የሙጥኝ ማለቱ መልካም ነው። ይኽ እንዳለ ሆኖ ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ከእናንተ መከራን የሚቀበል እርሱ ይጸልይ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር እርሱ የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደርሱ ይጥራ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል ኃጢያትም ሠርቶ እንደሆን ይሰረይለታል በማለት የተናገረው ቃል አለ ይኅ በቤተክርስቲያናችን ሚሥጢረ ቀንዲል በመባል ይታወቃል የንስሃ አባታችሁን በመጥራት አስቀድማችሁ ቤት ውስጥ ያላችሁ ሁላችሁ ንስሃን በመግባት ለእናታችሁ ሚስጥሩ እንዲፈጸምላቸው ማነጋገር መልካም ነው። ሚሥጢሩ የሚፈጸምበት የራሱ የሆነ ሥርዐት አለው። የቅዱሱ ሐዋርያ ቃል የታመነ ነውና ጌታም ባታምኑት እንኳ የታመነ ነውና ባለማመናችን አለማመኔን እርዳው በማለት ባለመታመናችን ይቅርታን እየለመንን የምንሻው ድኅነት ለሥጋም ለነፍስም ጠቃሚ እንደመሆኑ እናትህ እንደሚድኑ ተስፋ አደርጋለው። አይዞኽ ። እግዚአብሔር ይርዳችሁ። የያዕቆብ አምላክ ስም ብርታት ይሁናችሁ። ኪዳነምሕረት ትዳብስልኽ። በጸሎት እናስባችኋለን።
Jun 26, 2022