ምን መሰላችሁ የቤቱ ታላቅ እኔ ነኝ 19 አመቴ ነው ወንድ ነኝ ከእኔ በታች አንድ ወንድም አለኝ ከሱ በስተቀር እህትም ወንድምም የለኝም እና .. የዲግሪ ውጤት መቶልኝ በግል ኮሌጅ የጤና Field እየተማርኩኝ ነው , አባቴ ሹፌር ነው እናቴ የቤት እመቤት ናት ,,አሁን ከምንኖርበት ቤት ሌላ ባለሁለት መኝታ ቤት ኮንዶሚኒየም አለን እሱን ሽጠን አባቴ ራይድ እንዲሰራ እና በትርፍ ሰዓቴም ከቻልኩ እኔም እያገዝኩት እንድሰራ አማከርኩት ...ነገርግን እሱ ጭራሽ አለተቀበለኝም በዛ ላይ ደግሞ በአሁኑ አመት መጨረሻ ጡረታ ይወጣል plus ደግሞ ማታ እየደከመው ይገባል ጠዋት 12 ሰዓት ይወጣል በጣም እያሳዘነኝ ነው ..እንዴት አድርጌ ላሳምነው በተለይ አባታችሁ በዚህ ላይፍ ውስጥ ያሳለፈ ካላችሁ ሀሳባችሁን ስጡኝ ASAP
Jun 22, 2022ለአባትህ ማሰብህ እንዳለ ሆኖ ግን አሁንም አሱ አባትህን መሆኑን አትርሳ። አባት የሚያስበው ስለዛሬ ብቻ ሳይሆን ስለነገም ያስጨንቀዋል። "ዛሬ ቤቴን ከሸጥኩ ልጆቼ ነገ እራሳቸውን ሲችሉ የት ይኖራሉ?" የሚለው ራሱ ያሳስባቸዋል። ስለዚህ ስማኝ ወንድሜ። አባትህ እስከሚደክመው ድረስ የሚሰራው ለልጆቹ የዕለት እንጀራ ሲል ነው፥ ይህ በማረጉም ምንም ያህል አድካሚ ይሁን እንጂ አባታዊ ኃላፊነቱን በመወጣቱ ደስተኛ ነው። ነገ ለሚገኘው እንጀራ ብሎ ጎጆን መጣል ደሞ ወደ ውድቀት እንጂ ወደ ልቀት ሊመራ አይችልም። ስለዚህ በዚ ነገር አባትህን ለማሳመን ባትሞክር ጥሩ ነው። ከዛ የሚያገኘው የቤት ኪራይና የጡረታ ገንዝብ ሁሉን ነገር ያሟላል ባይባልም ግን በቂ ነው።
Jun 22, 2022