ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ በጣም ስለጨነቀኝ ነው ቢያንስ እናንተ እንድታማክሩኝ ነው የሲጋራ ሱስ አለብኝ ጠዋት ስነሳ ያምረኛል ግን ደግሞ ላለማጨስ ውስጤ ይፈልጋል ግን ደግሞ አብረውኝ ያሉ ሲያጨሱ ካየው አጨሳለው እና እንዴት ላቆም እችላለው
Jun 19, 2022ሰው እንደ አዋዋሉ ነው። ከምትውለው ሰው ጋ ነው ምትመሳሰለው። ለዛ ከሚያጨሱት ጋ አትዋል። ስለሱ እንድታስብ የሚያደርግህን ሀሳብም ሆነ ነገር ላለማሰብ ሞክር። ግን ከመጣብህ ቶሎ ሀሳብህንም ድርጊትህንም ቀይረህ ራስህን በየሆነ ነገር 'ቢዚ' አድርግ። ሁኔታህ ላይ ባለመሆኔ ላይገባኝ ቢችልም ይህ ሊጠቅምህ ይችላል።
Jun 20, 2022