በግል ኮሌጅ የጤና ፊልድ እየተማራችሁ ቢሆን እና ቤተሰብ(እናታችሁ ) ሰዎችን አማክራ ካሜራ ማንነት እንድትማሩ እና ተምራችሁ ስትጨርሱ ደግሞ ሙሉ ስቱዲዮ መክፈቻ ብር እንደሚሰጣችሁ ቢነገራችሁ . እና አሁን የምትማሩትን የጤና ፊልድ ትተውታላችሁ ወይስ ወደ ሁለተኛውን አማራጭ ማለትም እናታችሁ ያለችውን ታደርጋላችሁ ?...እውነት እንደው የፎቶ ሙያ አዋጭ ነው በዚ ሰዓት ብላችሁ ታስባላችሁ? (በነገራችን ላይ ከጠቀማችሁ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፣19አመቴ ነው እና ወንድ )
Jun 17, 2022የእናትህ እገዛ መኖሩ ጥሩ ነገር ነው። ከዛ በፊት ግን ቀልብህ ያለው ወዴት ነው? አንተ የጤና ባለሙያ መሆን ትፈልጋለህ? የመሆን ፍላጎትህ ከፍተኛ ከሆነ ጤና ትምህርትህን ካጠናቀቅክ በኋላ እናትህ ያለችልህን ተማር። ግን ደሞ የጤና የምትማረው አማራጭ በማጣት ወይም ያለ በቂ ፍላጎት ከሆነ የእናትህን offer ተቀበል።
Jun 18, 2022