✋ Hi sewoch ine demo andin lij afekerkuat ina isuwam indafekerchign tinegraygnalech gin laminat alchalkum demo be silk ke bizu sew gar taworalech ine demo litawat bil afkiryatalewu demo isuwam ine keante maninm alafekerkum minamn tilalech gin ke bizu wond taworalech like be imo be voice be SMS ina min largat litewat woys limenat??
Jun 17, 2022. . እባካችሁ እዚ ላይ Relationship በተመለከተ ጥያቄ የምትጠይቁ ሰዎች በጠቅላላ ወንድማዊ ምክሬን ብታደምጡ ደስ ይለኛል ይህን ስል ለእናንተ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለሚያነቡትም ለሚሰሙትም ነገ ላይ ለሚመሰርቱት የፍቅር ግንነኙነት ጥቅም ስል ጭምር ነው። በቅድሚያ የልብ አምላክ ዳዊትን ቃል ላስቀድም "አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር ወውኅደ ሃይማኖት እምዕጓለ እመሕያው" አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልና ከሰው ልጆችም#መተማመን ጎድሏልና ።ይህን ቃል ልብ በሉ። ዘመናችን በማንኛውም ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር እርስ በርሳችን የማንተማመንበት መሆኑን በቅድሚያ #አስተውሉ። በትዳር በስራ በፍቅር በጓደኝነት በጉርብትና በማንኘውም ሁኔታ ውስጥ እርስ በርስ መተማመን የሚባል ነገር የለም። በህግ ፊት እንኳ ከክቡሩ የሰው ልጅ ይልቅ ብጣሽ ወረቀት ተቀባይነትና ተአማኒነት እንዲኖረው ያደረገው የሰው ልጅ ከሰውነቱ የመዝቀጡ ውጤት ነው። ይህ እንዴት ሆነ ? ከንቶ ይትናገሩ አሐዱ ምስለ ካልኡ በከናፍረ ጉሕሉት ልበ ወበልብ ይትናገሩ።(እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ ) ሌላውን ልተወው አንዷን ነጥቤን ነጥዬ ልግለጥ በማንኛውም ሚዲያና ድኀረ ገጽ ላይ የሚለጠፉ ልጥፎች የሚወሩ ወሬዎች የሚጠየቁ ጥያቄዎች የወጣቶቹ ሁኔታ በጠቅላለው አንዳችን ሌላችንን እንዳናምንና በመሀከላችን መተማመን እንዳይኖር የሚያደርጉ ናቸውና እንዲ አይነት ነገሮችን ከማየትም ከመስማትም መቆጠብ አስፈላጊ ነው። #ከልባችሁ_የሌለን_በአንደበታችሁ_አትሸንግሉ። #ለከንቱና_እንደ_እንግዳ_ደርሶ_ለሚመለስ_የሥጋ_ፍላጎት_የሥላሴን_መቅደስ_አታፍርሱ። #አልታመንኩም_ብላችሁ_አትጩኹ_ታምናችሁ_ተገኙ። #ከእውነት_ጋር_ስለ_እውነት_ቁሙ_በነፈሰበት_አትንፈሱ። #ጠዋት_አስቀድሳችሁና_ዘምራችሁ_ማታ_አትዝፈኑ። #ሀገር_ውደዱ_እኔነት_ትታችሁ_እኛነት_ልመዱ። #ሰውን_በሰውነቱ_አክብሩ_በስብዕናው_ውደዱ_በሚጠፋው_በዓለም_ሚዛን_ሰውን_መዝናችሁ_ቦታ_አትስጡ። ከእውቀት ሳይሆን ከፍፁም ፍቅር ይኽን አልኩ ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት። በእንባና ኀዘን በእግር ጉዞ ላይ የተጻፈ እሺ ብትሉ የምድርን በረከት ትበላላችሁ። By: Mikopia 👨 🎖 2710 rep an hour ago
Jun 18, 2022