ሰብዓዊነት የጎደለው አሰራር
Jun 17, 2022የአዲስ አበባ ፖሊስ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል። ፖሊስ ድርጊቱ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ መፈፀሙን ገልጿል። ተማሪው በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ መሄዱን ከዛም በኃላ አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል እንደፈፀሙበት አስረድቷል። ህገ- ወጥ ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ በደረሰው መረጃ እና ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት ተማሪው ርችት እንደተኮስ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ፖሊስ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል ብሏል። ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል። በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
Jun 17, 2022#Update የአዲስ አበባ ፖሊስ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል። ፖሊስ ድርጊቱ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ መፈፀሙን ገልጿል። ተማሪው በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ መሄዱን ከዛም በኃላ አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል እንደፈፀሙበት አስረድቷል። ህገ- ወጥ ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ በደረሰው መረጃ እና ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት ተማሪው ርችት እንደተኮስ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ፖሊስ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል ብሏል። ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል። በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ @tikvahethiopia
Police violence
Jun 17, 2022