How can one protect themselves from witchcraft (ጥንቆላ)? I’m Orthodox Christian girl. I used to be so naive I would eat at everybody‘s house, borrow everyone my clothes, I even gave my friend my sport bra once. My mom is super into this stuff like she watches a lot of YouTube videos mnamn and she’s very concerned that somebody (from our family) has done something to me. I’m at a point where I don’t even like receiving gifts because I’m afraid and also giving stuff to people. I really don’t trust anyone anymore. I just want to protect myself and want to know what I can do against it besides praying?
Jun 10, 2022በጣም ያሳዝናል። እውነተኛ ኦርቶዶክስ ከሆንሽ ምክሬን ስሚ እየመረረሽም ቢሆን ዋጪው። በቅድሚያ ማመን ያለብሽ የሰው ልጅ ጥበቃ የሚሻ መሆኑን ነው ዳዊት እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዘብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል በማለት ሰው ቤትንም የሚሰራው ሀገርንም የሚጠብቀው ራሱም የሚጠበቀው በእግዚአብሔር ቸርነትና ጠባቂነት በመሆኑ እንዲ ካለ ነገር ራስሽን መጠበቅ እንዴትም አትችይም አንቺ ፍግ ዲያቢሎስ እሳት አንቺ ምድራዊ ዲያቢሎስ ሰማያውዊ አንቺ ግዙፍ ዲያቢሎስ ረቂቅ መሆናችሁን መርሳት የለብሽም። እንደ አፈ ቅቤ ሰባኪ ሰይጣን ኃይል የለውም እልል በይ አልልሽም ግጥም አድርጎ ሰይጣን ኃይል አለው። ኃይል ያለው ግን በማይጾም በማይጸልይ በማይሰግድ በማይመጸውት ከምንም በላይ ደግሞ ንስሀ በማይገባ ሰው ላይ ኃይሉ በሰውየው ግብር ይታወቃል። ልብ በይ። አንቺ ይኸን የዲያቢሎስን ኃይል ተመልክተሽ ራስሽን ለመጠበቅ ስትይ ሰው አታምኚም ስጦታ አትቀበይም እቃ ላለመስጠትም ወስነሻል በአጠቃላይ ራስሽን ለማዳን መላ ፈለግሽ እንደው መላ ብታገኚ በእግዚአብሔር መመካትሽን ወዲያ ትተሽ በብልሀትሽ ልትድኝም አይደል ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ ኃይለኛም በኃይሉ አይመካ ባለጠጋም በገንዘቡ አይመካ የሚመካ ታዲያ ሁሉን ባስገኘ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎልንስ የለ ? ከዲያቢሎስ ከሰዎች የጥንቆላ አሰራር ለማምለጥ በዚህ መልኩ እንዲ የተጨነቅሽው #ለምን እንደሆነ ታውቂያልሽ ? #አንቺም #እናትሽም የእግዚአብሔርን ኃይል ከመመልከት ይልቅ ከንቱ የአጋንንትን የምስክርነት ልፍለፋ በማዳመጥ ግዜአችሁን በከንቱ ስለምታጠፉት ነው። ምናለ እናትሽ ይህን ከምትከታተልና ያንቺንም አይምሮ ከምታስጨንቅ በቅጡ ቤተክርስቲያን ሄዳ ብትማር ( እየሰደብኳት እንዳይመስልሽ እየገሰጽኳት ነው። ንገሪያት ከንቱ የአጋንንት ልፍለፋ ማደረመጥሽን አቁሚ ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት አይጠቅሙሽም በያት ) ይቺ ይቺ የነ ግርማ የነ ሔኖክ የነባህታዊ ነን ስራ ናት ። የጠላትን ኃይል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ኃያልነት ተማሪ/ሩ ራስሽን ጠብቀሽ የት እንደምትደርሱ እናያለን ከማ ተስማማታችሁ እንደምትኖሩም እናያለን።መጽሐፍ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ብሎ ሳለ ሰውን ሁሉ የጎሪጥ በጥርጣሬ እየተመለከቱ ክርስትና የለም። ዲያቢሎስማ አንዴ ሊውጠን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችን አይደል ውጊያችን ከስጋና ደም ያይደለ ከጨለማው አበጋዝ እንጂ። የሆነ ሆኖ እንዲ ያለ ሀሳብ ከአይምሮሽ አንቺም እናትሽም አውጡ ጹሙ ጸልዩ ስገዱ ቁረቡ። ሥጋወ ደሙ በድድ ጀምራችሁ በድድ አትጨርሱ። ለጆሮ ለዐይን የሚገባውን ስጡት። (ሴት ነሽ እንዳየውሽ ሴቶች ራሳችሁ አጋንንት ሆናችሁ አጋንንት አትሽሹ። ምንዝር ጌጥ አታብዢ ትውዝፍት ምን ምን አጋንንትን መምሰል ነው። ሰው መተት ባይሰራብሽ ራሱ እነዚ ነገሮች አጋንንት ይስባሉ ተጠንቀቁ)
Jun 11, 2022