selam esti helm meftat mechil kale betly Muslim eht wendemoche be helm ኒቃብ betadergena sewch sidenegetu betay mndenw tergumu
Jun 05, 2022السلام عليكم ህልምን በኢስላም ትልቅ ቦታ ያለውና ወደፊት በህይወታችን ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን በጨረፍታ የምናውቅበት ነው። ያየሽውን ህልም ለምትቀርቢው/ክፉሽን ለማይመኝ ወይም ለህልም ፈቺ መናገር እንጂ ለተራ ሰው መናገር አያስፈልግም። በተለይ አላህ ባንቺ ላይ ለሰጠሽ ኒዕማ በድብቅ ምቀኛ የሚሆንብሽ ብዙ ሰው በመኖሩ ህልምሽን በፍፁም ማባከን የለብሽም!! ህልም በአመት አንዴ እንኳ የሚያዩ ባለመኖራቸው ህልም በማየትሽ ራሱ የሚመቀኙሽ ብዙ ናቸው። ስለዚህ ህልምሽን በትክክል ይፈታልኛል ብለሽ ለምታስቢውና ለወላጆችሽ ብቻ መናገርሽ ይበቃል። ሌላው ትርፍ ነው። ህልምም ሲፈታ ('ፈ' እና 'ታ' ይጠብቃሉ😁) በጣም ጥንቃቄ ይፈልጋል። ብዙ ሰው ትኩረትም አይሰጠውም። እኔና ቤተሰቦቻችን እያንዳንዱ እርምጃችን ማለት በሚቻልበት ሁኔታ በምናየው ህልም ነው። አንድም ህልም አናይም ከህልሙ በኋላ እርምጃ የምንወስድ ብንሆን እንጂ። በዚህም አላህ እኛን ከብዙ ጠላቶቻችን አትርፎናል። ብዙ መልካም ነገሮችንም አይተናል። እኔ በአቅሜ በህልሜ አይቼ በቀጣይ ጊዜያት አንድ በአንድ ምንም ለውጥ ሳይኖረው በተግባር የሆነልኝ ብዙ አጋጣሚ አለ። ለዚያ በህልሜ አልቀልድም። ረሱልም (ሰዐወ) በመጨረሻ ዘመን የሚታዩ ህልሞች ለእውነት የቀረቡ እንደሆኑም ነግረዉናል። እንዲሁም ሸይኽ ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው) አብዝተን በህልም እንዳንደገፍም መክረዉናል። ምክንያቱም ሰይጣን ይህን በመጠቀም እንድንቃዥ በማድረግ የፍርሃት ህይወትን እንድንኖር ስለሚያደርገን። ጥሩ ህልም ካየሽ ጥሩ፤ መጥፎ ከሆነ ግን 'አዑዙ ቢላህ' ብሎ ከሀሳብ ማራቅ ነው። ወዳንቺው ህልም ስመጣ ለጊዜው ከኢንተርኔት ይህን አግኝቻለሁ። "يقول ابن شاهين، إن النقاب في المنام هو دليل على العفة وعلى الستر في الحياة، كما انه دليل على الرزق الوفير وعلى الخير الكثير وسعي الرائي من أجل تحقيق الأهداف في الحياة. رؤية ارتداء النقاب في منام العزباء هو دليل على التدين والعفة والشرف، وهي دليل على الستر وعلى الزواج عن قريب من رجل سوف يحافظ عليها وسوف يحبها كثيرًا." አባቴ የህልም ፍቺ መፅሀፍ አለው። እሱን ሳገኝ ፎቶ አንስቼ እልክልሻለሁ። በተረፈ ጥሩ ህልም ፈቺ ብታገኚ በብዙ መንገድ ይፈታልሽ ነበር። ለምሳሌ -በህልም ኒቃብ የለበሰችው በእውኑም ኒቃብ ለባሽ ነች አይደለችም? -ለባሽ ከሆነችስ ለአላህ ብላ ነው የለበሰችው? ወይስ ወንጀል ሰርታ ከነበር ከወንጀሉ ለመደበቅ? ወይስ ቆንጆ ስላልሆነች? ወይስ ቤተሰብ ስላስገደዳት?... -አላህን የምትፈራና ወንጀል የማትዳፈር ነች አይደለችም? -ይህን ህልም በዛ ሌሊት ከማየቷ በፊት ቀን ላይ ስለ ኒቃብ ያወራችው ወይ ያሰበችው ነገር ነበር? -በህልሟ ስትለብሰው ሙሉ የኒቃብን ህግ የጠበቀ ነበር ወይስ ጎዶሎ ነገር ይታይባት ነበር?( ከፊል ፊቷን ወይ ፀጉሯን ማሳየት፣ የተቀደደ መሆኑ...) -በህልሟ ኒቃቡን ባደረገችበት ሰአት ቀን ነበር ወይስ ምሽት?... ብዙ ጥያቄዎች አሉት። በተረፈ በጥቅሉ ኒቃብ መልበስ ከላይ እንደተፃፈው ኸይር ነው። ብዙ አወራሁ። አላህ ለአባቴ ህልምን የመፍታት ጥበብ ስለሰጠው ከሱ ትንሽም ቢሆን ተምሬያለሁ። ለዛ ነው። ዐፍወን!
Jun 06, 2022