እንዴት ዋላችሁ/አመሻችሁ በዚኽ ላይ ምላሽ የምትሰጡ ሰዎች የምትጠይቁ አይታችሁም ዝም ብላችሁ የምታልፉ ሁላችሁ እስኪ በወንድማዊ ፍቅር አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ፍቃዳችሁ ሆኖ የምታነቡት ሁሉ ምላሽ ብትሰጡኝ ምነኛ ደስ ባለኝ የሆነ ሆኖ ግን አላስገድዳችሁም ለፍቃደኞች ግን ጥያቄዬ ይኽ ነው. .ሳትዋሹ ሳትደብቁ ስለራሳችሁ የሚሰማችሁን እውነት አጋሩኝ በሕይወታችሁ በስራችሁ በአነጋገራችሁ በአለባበሳችሁ በማንነታችሁ ደስተኛ ናችሁ ? ስለራሳችሁ ምንድነው የሚሰማችሁ . . .ምን ይጠቅመሀል እንዳትሉ ባልመልስላችሁም ለጋራ ጥቅማችን ስለሆነ በቅንነት እውነቷን ቁጭ እናድርግ። ሴቶችም ወንዶችም ጉራውን ምናምን ወዲያ ጣሉት። አመሰግናለው
Jun 04, 2022ደስታ አንጻራዊ ነው! ለአንዱ የደስታ ምንጭ ለሌላው ሃዘን ወይም ቅንጦት ሊመስል ይችላል፡፡ እኔ ግን በብዙ ነገር ደስተኛ አይደለሁም እስፔሻሊ በሃገሬ እና በእንደዚህ አይነት ውጥንቅጥ ወስጥ ልጅ በማምጣቴ ደስተኛ አይደለሁም ንግግር አለባበስ ማንምን ለኔ አይሞቁኝም አይበርዱኝም ብዙም ኬረዳሽ ነኝ ለማቴሪያሊስቲክ ነገር ያ ማለት ግን አልጠቅርምም እያልኩ ሳይሆን ቢመጡም ቢቀሩም ደስታዬ ላይ ልዩነት አያመጡም ከዛ ይልቅ በዙሪያዬ ያሉት ነገሮች ላይ ባለኝ አቅም ፈሰስ ሳደርግ በሚፈጥሩት ደስታ ውስጤ ይፈነጥዛል ከዛ ውጪ በሃይማኖት ረገድ ጠንካራ ባለመሆነ በጣም አዝናለሁ ብዙ አሳልፊያለሁ ግ ን እንደድሮው ጠንካራ አይደለሁም ለዛ ምክንያቶች ይኖሩኛል ነገር ግን ለችግሬ ማላከክ ስለሚሆንብኝ እንለፈው በደፈናው ሰንፊያለው በሚል ሙሉ ሃላፊነቱን ልውሰድ... ሌላ ምን ቀረ 🤔 ይበቃል ላሁኑ እያየን እንጨምራለን 😅
Jun 04, 2022