Make out ena sex chat yarege sew be sreate teklil magbat yechlal ende ergetegna yehonachubetn becha negerugn
May 29, 2022ግለ ወሲብ / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል? #ካለፈው_የቀጠለ ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈትታ የኮበለለች ሴት ናት። ከሄደችበትም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾትና ክብር ነው። አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም። ማለትም ኃጢአት ሠርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀምኩት እያለ ስለ በደሉ ያለቅስ ነበረ እንጂ የገነት ተድላ ደስታ ቀረብኝ እያለ ስላጣው ነገር አያዝንም ነበር። " አልቦቱ ካልዕ ሕሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ" ሰለ ኃጢአቱ ከማልቀስ በቀር ለአዳም ዘእንበለ ብካይ አልነበረውም። የተባለው ሰለዚህ ነው። እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተስነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን? ተክሊልስ ይገባኛል? " እያለ ያጣውንና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ " አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ።" (መዝሙረ ዳዊት 51: 4) ማለት ኃጢአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ይባላል። በመጨረሻ ከማስተርቤሽን እና ይህንን ከመሰሉ የዝሙት ርኩሰት መንገዶች የምታመልጠው በተቀደሰው ጋብቻ አማካኝነት ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ፦ " ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7: 2) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዝሙትን ጠንቅ ብሎ ነው የጠራው በወጣትነት ወራታችን ከዲያብሎስ ከሚወረወሩ ፍላጻዎች መካከል አንዱ የዝሙት ፍላጻ ነው ይህንን ፍላጻ ለመመከት ጋብቻ መመከቻ ጋሻ መሆኑን ከገጸ ንባቡ እንረዳለን። በእውነት ከሴጋ የኃጢአት ዓለም ወጥተን በተቀደስ ጋብቻ ለመኖር ማሰባችን የሚመሰገን መንፈሳዊ ውሳኔ ቢሆንም ጋብቻችንን ግን በትህትና በተሰበረ ልብ ልንፈጽም መዘጋጀት ይኖርብናል። አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል። እነዚህ ሰዎች ሰለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆናቸውን አጉልተው በማምታታት /በማድበስበስ/ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለመአት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ተወዳጆች ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ያስከትላል ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለው " የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።" (መዝሙረ ዳዊት 19: 13) ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ሰለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፍጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ አይገባኝም ልንል ያስፈልጋል። #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️ By: Anonymous 🎖 41 rep 20 hours ago
Jun 02, 2022