26 አመቴ ነው ከ 9 አመቴ ጀምሮ ያደኩት ጎዳና ላይ ነው ከዛም በበጎ አድራጎት በኩል ት/ት ተማርኩና ከዛ ህይወት ለመውጣት ቻልኩ። ክፍለ ሀገር እያለሁ በልጅነቴ አባቴ የእኔ ልጅ አይደለም ብሎ እናቴን በእርግዝናዋ ከቤት አባሮ ሌላ እንዳገባ እኔንም ተወልጀ በሰወች አማላጅ ቢጠየቅም አይ ልጄ አይደለም እንዳለ እናቴም እስከ 9 አመቴ እንጨት እየሸጠች አሳደገችኝ። አባቴ ይኑር ይሙት አሁን አላቅም ማወቅም ማግኘትም ፍላጎቴ አይደለም። በሱ ስም መጠራቴም እስካሁን አልወደውም አልፈልግም እና እባካችሁ የአባቴን ስም ወደምፈልገው ስም መለወጥ የምችልበትን መንገድ ጠቁሙኝ። ከየት መጀመር እንዳለብኝና እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ። የምኖረው አዲስ አበባ ነው ወረዳ 2 ንፋስ ስልክ። ስለትብብራችሁ አመሰግናለሁ።
May 21, 2022ፍርድ ቤት ሂጂ ማመልከቻ አስገቢ(እዛው ሚፅፉ አሉ)
May 21, 2022