ሰላም ሰወች እንዴት ናቸው። ምን መሰላችው፤ እና ድሮ ድሮ ምንም ነገር አያልበኝም ነበር። ነገር ግን ከ16 አመቴ ጀምሮ በጣም ነው የሚያልበኝ 💦😓😰። ሲጀምረኝ ቲንሽ ቲንሽ ነበር የሚያልበኝ ከግዜ በኋላ ግን እየበዛ ነው የሚሄደው። አሁን 23 አመቴ ነው። ነገር ግን በጣም ነው የሚያልበኝ። ሰውነቴ ውስጥ ምንጭ እንዳለ ነው የሚሰማኝ። የተወሰነ ርቀት ከተጓዝኩ በቃ ሰውነቴ ላብ በላብ ነው የሚሆነው። ፕረዘንቴሽን ሳደግ መላ ሰውነቴ በላብ ነው የሚጠመቀው። ከሰው ጋር ሳወራ ላብ በላብ ነው የምሆነው። እና በዚህ ምክንያት ከሰው ጋር አብሮ መሆነንን እጠላለው። ብቻየን መሆንን ነው የምመርጠው። በዚህ ምክንያት አሁን ላይ በጣም ድብርት ስሜት እየተሰማኝ ነው። መፈጠሬን እንኳን እስክጠላ ድረስ ነው፤ ተጽዕኖ የፈጠረብኝ። አሁን መማር አልቻልኩም፤ መስራት አልቻልኩም በቃ ህይወት ጭልም ነው ያለብኝ። በዚህ ሁኔታየ ወደፊት ምንም አይነት ተስፋ እንኳን አይታየኝም። አንዳንዴ አሁን ሞቸ ብገላገል ብየ እመኛለው። 😭😭😭 እና እባካችው ለዚህ ነገር መፍትሄ ካለው፤ ዶክተሮች የጤና ባለሙያወች ካላችው እባካችው እርዱኝ።
May 17, 2022ሰላም አሁን እንዴት ሆንክ በናትህ እኔም በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ነኝ😭😭
Feb 22, 2025