ይህ ጥያቄ ለሙስሊሞች ነው ። እንደሚታወቀው ክርስትና በ4th century ወይም ከዛ በፊት የነበረ እስልምና ደግሞ ከ7th century በኋላ የመጣ ነው። እናም የእኔ ጥያቄ እናንተ የኛ ሃይማኖት ብቻ ልክ ነው የምትሉ ከሆነ እንዴት የእናንተ መጽሐፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር ሊቀራረብ ቻለ? ብዙም ሆነ ትንሽ እንዴት የትም የማይገናኙ ሃይማኖቶች መጽሐፍ ታሪካቸው ተቀራረበ?
May 17, 2022ጥሩ ጥያቄ ነዉ፡፡ በ ቅድሚያ ግን ኢስላም ከ 7ኛዉ ክፍለዘመን በኀላ የመጣ ሳይሆን የሰዉ ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ማለትም ከ አደም እና ከሀዋ ጀምሮ የነበረ የሁሉም ነቢያት ሀይማኖት እንደሆነ ነዉ የምናምነዉ፡፡ በ ኢስላም አስተምህሮ መሰረት ሁሉም ነቢያት " ከ አላህ ዉጪ በ እዉነት የሚገዙት እና አምልኮት የሚገባዉ አምላክ የለም፤ ከእርሱ ዉጪ የምታመልኳቸዉን ጣኦታትንም ራቁ" የሚል መሠረታዊ መልእክትን ለማስተላለፍ ነዉ ወደየ ህዝቦቻቸዉ የተላኩት፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው አሏህ ነብያትን ሲልክ ከእነርሱ ጋር አብሮ መመሪያ ይሆናቸዉ ዘንድ መፃህፍትንም ያወረደበት አጋጣሚዎች አሉ ለምሳሌ:- ለ ዳዉድ ወይም ዳዊት ዘቡርን ፣ ለ ሙሣ (ሙሴ) ተዉራትን ፣ ለ እየሱስ ኢንጂል(ወንጌል)ን ፣ ለ አብረሃም ሱሁፍን እና ሌሎችንም መፃህፍት ልኳል፡፡ so originally እነዚህ መፃህፍት ከ ፈጣሪያችን አሏህ ለሠዉ ልጆች መመሪያ ይሆኑ ዘንድ የተወረዱ ናቸዉ ማለት ነዉ፡፡ ምናልባትም ከ ዝርዝር ጉዳዮች ዉጪ ያለዉ መሠረታዊ መልእክት ተመሣሣይነትም ከዚህ አንፃር ነዉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነቢያት ካለፉ በኀላ ፤ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ .....ህዝቦቻቸዉ መንገድ እየሳቱ ፤ ከ ሀይማኖቱ አስተምህሮ ይልቅ በሀይማኖት ካባ ስሜታቸዉን እየተከተሉ የ ሀይማኖት መፀሀፍቶችን ሳይቀር ለስሜታቸዉ እና ፍላጎቶቻቸዉ እንደሚሆን አርገዉ ቀደዉ መስፋት ፣ ቆርጠዉ መቀጠሉን ተያያዙት፡፡ በ ዉስጡ ያሉት ምዕራፎች(መፃህፍት) 66 ይሁኑ 73 እንኳን መለየት እስከማይቻልበት ደረጃ የደረሱ መፃህፍት እንዳሉ ልብ ይሏል፡፡ ለዚህም ሲባል ክብሩ የላቀዉ የሁሉ ፈጣሪ አሏህ ለሠዉ ዘር በሙሉ እዝነት ተደርገው ለተላኩት የመጨረሻው ነቢይ ለነቢያችን ሙሀመድ (ሠ.ዐ.ወ.) ዘላለማዊ ተዓምር ይሆን ዘንድ የተከበረዉ ቃሉን ቁርዐንን ለሠዉ ልጆች መመሪያ እና መድሀኒት ይሆን ዘንድ እርሱን መሠረዝ ፣ መደለዝ ፣ መለወጥ የማይቻል ሲሆን ያወረደዉ፡፡
May 17, 2022