Hello guys Yne tiyake mn meslachu i want to know about islamic religion...ene awn bergit mnm religion teketat aydelewm...gn sile islam mawek ena siletimertochu ena sirhatochu betam mawek efeligalew....so eskii tell me about it??
May 13, 2022ፈጣሪ/አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራህ ሀቢቢ። አሁን የምልክልህ ሁለት ቻናሎችን በደንብ ብትከታተል ስለ ኢስላም የጠለቀ እውቀት ይኖርሀል። የሁለቱም ቻናሎች ባለቤቶች በሀይማኖት ንፅፅር ላይ የጠለቀ እውቀት ያላቸው ናቸው። https://t.me/Yahya5 ያሕያ ኢብኑ ኑሕ ይባላል https://t.me/Wahidcom ወሒድ ዑመር ይባላል። ከቅርብ አመት ወዲህ እስልምናን የተቀበለ ሰው ቢሆንም በኢስላም ላይ እድሜያቸውን ያሳለፉ ሰዎች የማያውቁትን ሁሉ የሚያውቅ ባለ ምጡቅ አእምሮ ነው። ከክርስትናም የመጣ ስለሆነ ብዙዎቻቸው የማያውቁትን ያውቃል። ጎበዝ የሚያስብለው ዐረብኛ ግሪኪኛ አረማይክኛ እና የመሳሰሉትን ለቁርአንና ለመ/ቅዱስ በጣም ቅርብ የሆኑ ቋንቋዎችን ማወቁ ሲሆን ይህም ከሌሎች በተሻለ መልኩ መለኮታዊ መፃሕፍትን እንዲገነዘብ አስችሎታል። ከሁሉም የሚሻለው ደግሞ የአማርኛ ትርጉም ቁርአን ገዝተህ ብታነብና ያልገባህን ለሁለቱ ሰዎች ብትጠይቅ ያለምንም መወላወል መልስ ይሰጡሀል። የነቢዩ ሙሐመድን ታሪክ የሚተርኩ መፃሕፍትን ገዝተህ ማንበብም አትርሳ። ምክንያቱም በቁርአን፣ በኢስላምና በሙሐመድ ከሌላ እምነት ተከታዮች የሚሰነዘሩ ትችቶችን በትክክል ማየት ያስችልሀል። ማንኛውም ኢስላማዊ መፃሕፍት ቤት ገብተህ ስለ ነቢዩ ሙሐመድ የሚተርክ መፅሀፍ ብለህ ጠይቅ። ካልሆነ "ረሒቀል መኽቱም" ብለህ ግዛ እና አንብብ። ኢስላም ላይ ምስጢር የሚባል ነገር የለም። ምንም አይነት ጥያቄ ሲኖርህ እዚህ ሳይሆን በጉዳዩ ሊቅ የሆኑትን ሰዎች ብትጠይቅ ይመልሱልሃል። ምስጢር የሚባል ነገር የለም! ከሙስሊም ሊቃውንት ውጪ ብትጠይቅ ትክክል/የተሳሳተ መልስ ሊሰጡህ ይችላሉ። "ከባለቤቱ በላይ አውቃለሁ የሚል ጠንቋይ ነው" ይህን አትርሳ። በርታ! በውርስ የመጣ እምነትን መከተል ትተህ እውነትን ፍለጋ ላይ መታከትህ አርአያ እንድትሆን ያደርግሀል። አብሽር
May 14, 2022