በመጀመርያ ጽድቅ የሚለውን ቃል ትክክለኛ ትርጉም ማወቅ ይኖርብናል። ለብዙዎቻችን ጽድቅ ማለት መልካም ስራ ፣ ሕግን መጠበቅ ፣ ኃይማኖተኛ መሆን እና የመሳሰሉትን ነገሮች ይመስሉናል። ጽድቅ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ እግዚአብሔር ራሱ ብቁ ሲያደርግህ [ when God made you 'right' before him]። ወይም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ብቁ የሚያደርግ አንድ ባህሪ ወይም ተፈጥሮ ልንለው እንችላለን። አንድ ሰው ጻድቅ ስለሆነ መልካም ስራን ሊሰራ ይችላል ፤ መስራትም አለበት ። መልካም ስራ ብቻውን ግን ጻድቅ አያስብልም። ምክንያቱም አንድን ሰው ጻድቅ የሚያደርገው እግዚአብሔር ስለሆነ። የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር መብቱን በራሱ ምርጫ አጥቷል። ይህም ከእግዚአብሔር ለዘላለም እንዲለይ ምክንያት ሆኗል። እንግዲህ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብን ከወደድን ጻድቅ መሆን ይጠበቅብናል፤ በራሳችን ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ጻድቅ ማድረግ አንችልም። ታድያ እንዴት ነው ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን የሚያስችለንን ጽድቅ ምናገኘው...? ይህ ጽድቅ ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱን ጽድቅ እግዚአብሔር አምላክ የእኛ እንደሆነ የቆጠረበት እና የሆነበት ፤ የእኛ በደል እና ኃጢአት ደግሞ የኢየሱስ እንደሆነ እና እርሱ ሊቀጣ የሰውን ስጋ ለበሰ። እግዚአብሔርን ያስደሰተ ሰው ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንግዲህ ያለ እርሱ እግዚአብሔርን ማስደሰት የማይቻል ነገር ነው። ስለዚህ ይህ ጽድቅ እንዴት ይገኛል ? ስጦታ ነው እግዚአብሔር የሰጠን። በአንድ ልጁ በማመን ነው ይህ ዘላለማዊ እና አዳኝ ጽድቅ የሚገኘው።
May 13, 2022