Mnm aynet Muslim alneberem ende ke prophet muhammed befit Yet hidew new?
May 11, 2022በታሪክ መዛግብት ማንም ማንም ከ622 ዓም በፊት እስልምናን የሚከተል የለም። ከቁራን በፊት በተጻፉት መጽሃፍቶች እንደው እስልምና ስለሚባል ሀይማኖት አንዲት መስመር ላይ እንኳን ተጽፎ አይገኝም። እስልምና ከቁራን በኋላ ነው የተጅመረው ከ622ዓም በኋላ ማለት ነው። ሰው ሲወለድ እስላም አይደለም። ይሄ የሙሃሙድ ውሸት ነው። እስኪ አንደው አስቡት። እስልምና ከአዳም አንስቶ የነበረ እምነት ከሆነ። ነቢያት ሃይማኖታቸው እስልምና ከሆነ ስለምንድን ነው ስለ እስልምና ከቁራን በፊት በተጻፉት መጽሃፎች አንድም ቦታ ላይ እንኳን ያልተጻፈው?? በዛን ጊዜ የነበሩት፤ እነ አይውድ፤ ቡድሂዝም እነዚህን ታሪክ ያውቃቸዋል። እስልምናን ግን ከ622 በፊት ታሪክ በፍጹም አያውቀውም። ለምሳሌ በታሪክ ስለ ሂንዱይዝም ይታወቃል ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሃይማኖት ስለነበረ። ሂንዱይዝም ህይማኖትን የሚከተል ማህበረሰብ መሆሩን ከ2000 አመት በፊት በተጻፉ መጽሃፍት ማገኘት ይቻላል። ምክንያቱም ስለነበረ ማለት ነው። አይውድ እምነት በታሪክ መጽሃፍት ሰፍሮ እናገኛል፤ አይውድ እምነትም የሚከተሉ ሰወቻንዳሉ ከ2000 አመታት በፊት በተጻፉት መጽሃፍት ስለ አይውድ እምነት ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን በታሪክ ወደኋላ 2000 አመት አረ እንደው 1700 አመት እንጓዝ እና እስልምና የሚባል ሃይማኖት አለ ወይ ብለን እንጠይቅ?? ለምስላ በጊዜ ወደኋላ ተጓዝንና 200 ዓም ላይ ሄድን እንበል። እና እስልምና የሚባል ሃይማኖት አለ ወይ?? እስልምናን የሚከተል ማህበረሰብ አለ ወይ ብለን እንጠይቅ?? መጽሃፍትንም እናገላብጥ!! ግን እስልምናን የሚከትል ማህበረሰብ በ200 ዓም የለም። ስለ እስልምና የሚያወራ መጽሃፍም አናገኝም። አሁንም ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 100፤ 200፤ 300 ወዘተ አመታት በፊት በጊዜ እንመለስ። እና በዛን ግዜ እስልምናን የሚከተል ማህበረሰብ በፍጹም አይገኝም። በቃ ባጭሩ ስለ እስልምና ሃይማኖት የምናውቀው ከዛሬ 1400 አመት ወዲህ ነው እንጅ ከዛ በፊት እስልምናን የሚከትል ማንም ማህበረሰብ የለም።
May 12, 2022