ሰላም ለናንተ እባካችሁ ከዚህ መሀል ደራሲ የፅነ ፁሁፍ ባለሙያ ወይም የስነ አእምሮ አዋቂ ካለ እርዱኝ እባካችሁ የኔ ጥያቄ እስካሁን ቢያንስ ቢያንስ ከ 150 በላይ መፅሀፍትን አንብቤያለው ሊያውም ምርጥ ምርጥ የተባሉ ግን አሁን እራሴን ስጠይቀው ከነዚህ መፅሀፍት ምን አወኩ ስል ግራ ይገባኛል ቆይ ምንድነው ችግሩ ሌሎች መፅሀፍትንም ሆነ የትምህርት መፅሀፍትን ሳነብ ለጊዜው ይገባኛል እረዳዋለው ወይም አንድ ሌላ አሪፍ መፅሀፍ ሳነብ ከውስጡ ብዙ እማራለው በሌላ ጊዜ ግን የመፃፉ እርእስ ሁላ ይጠፋብኛል በእርግጥ መፅሀፍትን ሳነብ በጣም ደስ እያለኝ ነው ቆይ ችግሩ ምንድነው???? በቀናነት ንገሩኝ አመሰግናለሁ🙏
May 11, 2022የስነ አዕምሮ አዋቂ ሊረዳህ ይችላል ደራሲ ግን እንዴት ሊረዳህ እንደሚችል ግልፅ ባይሆንልኝም እኔ ከሁለቱም ያልሆንኩት ወንድምህ ግን ትንሽ ምክር ልለግስህ እፈልጋለሁ። ምን መሰለህ እኔም ብዙ የልብወለድ ስራዎችን አንብቢያለሁ ለጊዜውም ተዝናንቼበት ተምሬበታለሁም እና አሁን ላይ ዋና ገፀባህርያቱን እናኳ የረሳዋቸው ይኖራሉ።ትንሽ የሚያስታውሰኝ ሰው ካለ ግን አብዛኛው ምስጢሩ ይገለጥልኛል....እና አንድን መፅሐፍ ስታነብ ካንተ የሚፈለገው በመፅሐፍ መርካትህ እና መመሰጥህ እንጂ መሸምደድህ አይደለም።ምንም ደራሲው ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ሳይገባህ ሸምድደህ ማነብነቡንማ መፈለግ የለብህም ግን ይረሳኛል ላልከው በቃ ሰው ስለሆንክ ነው።🤷♂ይህ ግን ለልብወለዶች ነው። የሳይኮሎጂ ወይም የህይወት መምሪያ አይነት መፅሐፍትን ስታነብ ግን ተግባራዊ መምሪያዎች ስላሏቸው እነሱን በተግባር በማዋል ልምድህ ልታረጋቸው ይገባል እንጂ በጭንቅላትህ ተረድተህ ከ89አመት በኋላ ማስታወስህ ፍይዳ የለውም።ለምሳሌ፦ atomic habit , the success principles ....እና the secretንም ጨምሮ! የፍልስፍና መፅሐፍትን ስታነብ ደሞ ካንተ ብዙ ተምሰልስሎት እና ባነበብከው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ላንተ አሳማኝ እስኪሆንልህ የራስህ እስክታረገው ልታሰላስለው እና ልትመሰጥበት ይገባል። #በአጠቃላይ እውነተኛ ትምህርት የሚመጣው አዲስ መረጃ ስትይዝ ሳይሆን በድርጊት ስትገልፀው እና በዛም የባህሪይ ለውጥ ስታመጣ ነው።
May 12, 2022